ኢራን ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ሊገቡ የነበሩ ሁለት የአሜሪካ የጦር መርከቦችን መታሁ አለች

US Navy Destroyer

ኢራን የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ችላ ብለው ወደ ሆርመዝ ሰርጥ ሊገቡ የነበሩ ሁለት የአሜሪካ የጦር መርከቦችን (US Navey Destroyer) መምታቷን አስታወቀች።

ኢራን ይህን ያለችው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ መውጫ ተዘግቶባቸው በሰርጡ የቆሙ መርከቦችን አጅቦ እየመራ የሚያወጣ አንድ የባህር ኃይል ቡድን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው።

የአልጄዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው ግን “የኢራን የአሜሪካን የጦር መርከብ መታሁ” የሚለው መረጃ “ፈጠራ” ነው ሲል አጣጥሎታል።

አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ መጠነሰፊ የአየር ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ኢራን በአጸፋ በእስራኤልና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ባሉባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ የድሮንና የሚሳይል ጥቃት ስታደርስ ቆይታለች። ኢራን የአለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበትንና በደጇ የሚገኘውን የሆርሙዝ ስርጥን በመዝጋት በኢራንና አሜሪካ መካከል ያለው ጦርነት እንዲጦዝና ጦርነቱ አለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ ቀውስ እንዳያስከትል አድርጋለች።

ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ስታደርግ የነበረችው የሁለቱም ሀገራት ወዳጅ የሆነችው ፓኪስታን ተሳክቶላት የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሶ ነበር። ነገርግን ሁለቱም ሀገራት በሰርጡ ላይ የመርከቦች እንቅስቀሴ እንዳይካሄድ የጣሏቸውን እግዶች ለማንሳት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

አሜሪካ ኢራን ጦርነቱን ለመቋጨት የሚያሰችል የራሷን ሀሳብ እስከምታመጣ ድረስ በሚል የተኩስ አቁም የጊዜ ገደቡን ማራዘሟን አስታውቃ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ጦርነቱ በድጋሚ ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ ነው

Share this article

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *