- አፍሮ- ኢንሳይት ዜና
የኬንያ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት በራይላ ኦዲንጋ (Raila Odinga) ሞት ሃዘናቸውን እየገለጹ በነበረበት ግዜ፥ ከፖሊስ በተፈተ ተኩስ ሁለት ኬንያውያን ሲሞቱ ሶስት ኬንያውያን በተፈጠረው ከፍተኛ ግርግርና መረጋገጥ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ኬንያውያን በጆሞ ኬንያታ ስቴድየም ውስጥ ተገኝተው በተቃዋሚ ፖለቲከኛው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልጹ ነበርግርግሩ የተፈጠረው። ኬንያውያኑ በክፍት የሬሳ ሳጥን ውስጥ ባረፈው የኦዲንጋ አካል ፊት እያለፉ ሃዘናቸውን ገልጸዋል።
ኦዲንጋ፥ ደጋፊዎቻቸው “ባባ” ወይም በስዋሂልኛ “አባታችን” ብለው ይጠሯቸዋል። የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ፥ በሀዘን መግለጫው “ክቡር የህዝብ ልጅ አጥተናል” ሲል ተናግሯል። በ80 አመታቸው ህይወታቸው ያለፈው ኦዲንጋ ለpluralism (ብዝሃነት) እና ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ባደረጉት ትግል ይታወቃሉ።
የ1300 ኬንያውያንን ህይወት በቀጠፈው እና መቶ ሺህዎችን ባፈናቀለው የ1999 ዓ.ም ምርጫ ማግስት ኦዲንጋ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣንን አግኝተው ነበር። ምርጫውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመጽ፥ ኬንያውያን ዴሞክራሲን ይወክልሉናል ያሏቸውን ኦዲንጋን ወደ ስልጣን ያመጡበት አጋጣሚ ሆኖ ይታወሳል።
የእውቁ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ የሞት ዜና ከሰሞኑ የኬንያ ወጣቶች በአደባባይ ወጥተው ለሚያሰሙት የተቃውሞ ድምጽ ዳግም ማቀጣጠያ እንዳይሆን ተፈርቷል። ይህ ህዝባዊ ሃዘን ከቁጥጥር እንዳይወጣ በሚል የመንግስት የጸጥታ አካላት በከፈቱት ተኩስ ምክንያት ነበር አምስቱ ኬንያውያን የተገደሉት።
@afro_insight_news “ያለ አባት ቀርተናል!” ኬንያውያኑ አነቡ – አፍሮ- ኢንሳይት ዜና የኬንያ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት በራይላ ኦዲንጋ (Raila Odinga) ሞት ሃዘናቸውን እየገለጹ በነበረበት ግዜ፥ ከፖሊስ በተፈተ ተኩስ ሁለት ኬንያውያን ሲሞቱ ሶስት ኬንያውያን በግርግር ምክንያት ተገድለዋል። በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ኬንያውያን በጆሞ ኬንያታ ስቴድየም ውስጥ ተገኝተው በተቃዋሚ ፖለቲከኛው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልጹ ነበር ግርግሩ የተፈጠረው። ኬንያውያኑ በክፍት የሬሳ ሳጥን ውስጥ ባረፈው የኦዲንጋ አካል ፊት እያለፉ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ኦዲንጋ፥ ደጋፊዎቻቸው “ባባ” ወይም በስዋሂልኛ “አባታችን” ብለው ይጠሯቸዋል። የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ፥ በሀዘን መግለጫው “ክቡር የህዝብ ልጅ አጥተናል” ሲል ተናግሯል። በ80 አመታቸው ህይወታቸው ያለፈው ኦዲንጋ ለpluralism (ብዝሃነት) እና ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ባደረጉት ትግል ይታወቃሉ። የ1300 ኬንያውያንን ህይወት በቀጠፈው እና መቶ ሺህዎችን ባፈናቀለው የ1999 ዓ.ም ምርጫ ማግስት ኦዲንጋ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣንን አግኝተው ነበር። ምርጫውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመጽ፥ ኬንያውያን ዴሞክራሲን ይወክልሉናል ያሏቸውን ኦዲንጋን ወደ ስልጣን ያመጡበት አጋጣሚ ሆኖ ይታወሳል። የእውቁ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ የሞት ዜና ከሰሞኑ የኬንያ ወጣቶች በአደባባይ ወጥተው ለሚያሰሙት የተቃውሞ ድምጽ ዳግም ማቀጣጠያ እንዳይሆን ተፈርቷል። ይህ ህዝባዊ ሃዘን ከቁጥጥር እንዳይወጣ በሚል የመንግስት የጸጥታ አካላት በከፈቱት ተኩስ ምክንያት እና እሱን ተከትሎ በነበረው ግርግር ምክንያት ነበር አምስቱ ኬንያውያን የተገደሉት። #kenya kenyantiktok🇰🇪 #odinga #AfroInsight #news
♬ original sound – Afro Insight News











