Loading...

የቻይና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ፡ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር

China Investment in Ethiopia - China Ethiopia Relations

ቻይና የኢትዮጵያ ትልቅ የንግድ አጋርና ቀደሚ የውጭ ኢንቨስተር ነች። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን ባለፉት ሁለት አስርታት ውስጥ በፍጥነት በማደግ እአአ በ2024  4.9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል

ኢትዮጵያ ወደ ቻይና ቡና፣ ሰሊጥ፣ የቆዳ ምርቶች፣ የቅባት እህሎችና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ስትልክ ቻይና ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ማሽኖች፣ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድኃኒቶች፣ ጨርቃጨርቅና የግንባታ ቁሳቁሶችን ትልካለች። የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ቻይና በሚልካቸው ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር፣ የንግድ ሚዛኑን ለማሻሻል እየጣረ እንደሆነ ይገልጻል

የቻይና ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ለውጥ ዋነኛ ኃይል ሆኗል።

የቻይና ኢንቨስተሮች በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በግንባታ፣ በኃይል፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በማዕድንና በሎጂስቲክስ ዘርፎች በስፋት ተሰማርተዋል።

እአአ በ2025፣ ሽንዋ የተባለው የቻይና ዜና አለምአቀፍ ዜና አገልግሎት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ጠቅሶ 4500 የሚሆኑ የቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮጀከቶች ወደ ስራ መግባታቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ የስራ እድሎች መፍጠራቸውን ዘግቧል። ቻይና 50 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት(FDI) ድርሻ በመሸፈን ቀዳሚ መሆኗን የጠቀሰው ኮሚሽኑ፣ እአአ በሐምሌ 2024 በተጠናቀቀው የበጀት አመት ብቻ 3.92 ቢሊየን ዶላር የቻይና ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በወቅቱ በቅርብ አመታት ውስጥ 8.5 ቢሊየን ዶላር ያስመዘገቡ የቻይና ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ እና በማኑፋክቸሪንግ እና በሌሎች ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጿል። እነዚህ ፕሮጀክቶች 325,400 በላይ የሆኑ ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል መፍጠራቸውንም ኮሚሽኑ ጠቅሷል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው ፎረም፣ በአብዛኛው የቻይና የሆኑ ኩባያዎች 1.7 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ የማዕድንና ኃይል ዘርፉ ኢንቨስት ለማድረግ ውል አስረዋል።

የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት ዋነኛ ምሰሶ የሆነው ሌላኛው ዘርፍ የአቪዬሽን ዘርፍ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ50 ዓመታት በላይ በቻይና ገበያ በመሥራት ትልቅ ልምድ አካብቷል። በአሁኑ ጊዜ በሳምንት ከ35 በላይ የመንገደኞች በረራዎችን ወደ አምስት መዳረሻዎች ማለትም ወደ ቤጂንግ፣ ሻንጋይ፣ ጓንግዡ፣ ቼንግዱ እና ሆንግ ኮንግ ያከናውናል። በተጨማሪም ካርጎ(ጭነት) ወደ ስምንት መዳረሻዎች ያጓጉዛል። ይህ የሚያሳየው ቻይና የኢትዮጵያ አየርመንገድ ለሚሰጠው የመንገደኞችና የካርጎ ማመላለስ አገልግሎት ዋነኛ ገበያ መሆኗን ነው።

አየርመንገዱ የንግድ ጉዞዎችን፣ ቱሪዝምን፣ ኢንቨስትመንትንና የትምህርት ልውውጦችን ከማገልገል በተጨማሪ ቡና፣ አበባ፣ መድኃኒት፣ ጨርቃጨርቅና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ወደ ቻይና ያጓጉዛል። ከቻይና የሚመጡ ማሽኖች፣ ኤሌክትሮኒክስና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ወደ ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በማጓጓዝ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። አየርመንገዱ  እአአ በ2024/2025 ከፍተኛ የተባለ 7.6 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓመታዊ ገቢ አስመዝግቧል።  የቻይና ገበያ ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ይታመናል።

ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በታዳሽ ኃይል እና በአቪዬሽን ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ቀጣይነት ባለው መልኩ  እያጠናከሩ ናቸው ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰፊ የበረራ አውታር የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ከማጠናከር በተጨማሪ ለኢትዮጵያ፣ ለቻይና እና ለመላው አፍሪካ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ትስስር ወሳኝ ነው።

እአአ በ2026 የቻይና መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከመላው አፍሪካ ጋር ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ለመጨመር የዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ ይፋ አድርጓል። እአአ ከግንቦት 1፣2026 ጀምሮ ለ53ቱ የአፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ የሆነው ይህ ፖሊሲ ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶቿን ወደ ሰፊው የቻይና ገበያ በከፍተኛ መጠን እንድታቀርብና ገቢዋን እንድትጨምር ያስችላታል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው