Loading...

ቻይና አፍሪካ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎች ለመቀነስ እያደረጉት ያለው ትብብር ምን ይመስላል?

China–Africa climate cooperation New climate corporations

የአየር ንብረት ለውጥ በኢኮኖሚ እድገት፣ በምግብ ዋስትና፣ በስነምህዳርና በሰው ልጅ ጤና የጎላ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩና በ21ኛው ክፍለዘመን በጣም አሳሳቢ ከሆኑት ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው።  ምንምእንኳን አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላት አስተዋጽኦ ከ 4 በመቶ ያልበለጠ ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥ ለተጽዕኖ በድንበር የመገደብ  ባለመሆኑ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ለሚመጡ ችግሮች ተጋላጭ ሆናለች። በአህጉሪቱ ተደጋጋሚ ድርቅ፣ የሙቀት መጠን መጨመርና የደን ሽፋን መጠን መቀነስ ይስተዋላሉ።

ይህን ችግር ለመቀነስ አፍሪካና ቻይና ወደ ትብብር ከገቡ ቆየት ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራትና ቻይና፣ በቻይና-አፍሪካ ትብብር ማዕቀፍ( ፎካክ) ስር በታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታና በአረንጓዴ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ለመቀነስ ትብብራቸውን አጠናክረዋል

የታዳሽ ኃይል ልማት በአፍሪካ-ቻይና የአየር ንብረት ትብብር ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል በኢትዮጵያ የተገነባውን የአዳማውን የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጨምሮ በሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የውሃና የሶላር ኃይል ማመንጫዎች በቻይና የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ተሰርተዋል
እነዚህ ፕሮጀክቶች በነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ከመቀነስና የበካይ ጋዝ ልቀትን ከመቀነስ ባሻገር የኃይል አቅርቦትን ለማስፋት አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ሁለቱ ጉባኤዎች

እአአ በ2024 በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የፎካክ ጉባኤ፣ ላይ ቻይና ዘላቂ ልማትን ለመደገፍና የአህጉሪቱን የአረንጓዴ ልማት ሽግግር ለማፋጠን “30 የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክቶች ለአፍሪካ ይፋ” ማድረጓ ይታወሳል። ይህ ቻይና የታዳሽ ኃይል ትብብርን የሁለትዮሽ ግንኙነቷ ምሰሶ ማድረጓን ያሳያል።

በሥልጠና መርሃ ግብሮች፣ በቴክኒካዊ ልውውጦች እና በትምህርት ዕድሎች አማካኝነት የቻይና ተቋማት የአፍሪካ መሐንዲሶችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችንና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎችን በታዳሽ ኃይል፣ በአየር ንብረት ፖሊሲ እና በአካባቢ አስተዳደር ዘርፍ እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ ድጋፍ አድርገዋል።

የቻይና የውጭ ኢንቫይሮሜንታል ትብብር ማዕከል ምክትል ዳይሬተር ሊ ዮንግሆንግ  ከጉባኤው ቀደም ብለው “የአየር ንብረት ለውጥ ሁሉንም ሀገራት በጋራ መሥራት የሚጠይቅ የሰው ልጅ የጋራ ፈተና ነው። ቻይናም ሆነች የአፍሪካ ሀገራት በዚህ ችግር በእጅጉ ተጎድተዋል፤ በንቃትም ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ” ሲሉ ተናግረው ነበር። ይህ ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከአፍሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነት የገለጸችበት ነው።
በቤጂንግ ጉባኤ በፀደቀው የቤጂንግ መግለጫ(Beijing Declaration)፣ የቻይናና የ53 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች “የዓለም ሀገራት በሙሉ በአንድነት በመስራት፣ ክፍት፣ ሁሉን አቀፍ፣ ንጹህና ውብ፣ ዘላቂ ሰላም፣ የጋራ ደኅንነት እና የጋራ ብልጽግና የሰፈነበት ዓለም እንዲገነባ እንጠይቃለን”ብለዋል።

ከቤጂንጉ ጉባኤ ቀደም ብሎ እአአ በ1921 በዳካር በተካሄደው የአፍሪካ-ቻይና የአየር ንብረት ትብብር ጉባኤ፣ ቻይናና የአፍሪካ መንግስታት በታዳሽ ኃይል ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ  ተስማምተው ነበር። በጉባኤ ማጠቃለያ በወጣው የዳካር መግለጫ(Dakar Declaration ) “ሁለቱ ወገኖች ብቁ የተፈጥሯዊ ጋዝን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የመቀየር እና የአረንጓዴ ሃይድሮጂን ልማት ፕሮጀክቶች የአረንጓዴ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ ይደግፋሉ።” በጉባኤ ላይ አፍሪካና ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን በሚቀንሱ የታዳሸ ኃይል ፕሮጀክቶች ላይ ትብብር ለመስራትና የዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹበት ነበር። ቻይናም በአፍሪካ ሀገራት በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ በአቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልውውጥና ፋይናንስ በማድረግ፣ በጉባኤ የገባቸውን ቃል በተግባር አሳይታለች።

የአፍሪካ መንግስታት አቋም

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን የመቀነስ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረከኮች ሲገልጹ ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እአአ በ2025 በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ “ትክክለኛ ምርጫዎችን አሁን ካደረግን፣ አፍሪካ ሥነ-ምህዳሯን ሳታጠፋ ኢንዱስትሪያላይዝ የምትሆን የመጀመሪያዋ አህጉር ልትሆን ትችላለች” ብለዋል።

በተመሳሳይ የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ  አፍሪካን “ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ ወሳኝ አካል” እንደሆነች ገልጸው፣ ዓለም አቀፍ አጋርነቶች የአፍሪካን ግዙፍ የታዳሽ ኃይል አቅም እንዲጠቀሙበት እንጂ በአህጉሪቱ ተጋላጭነት ላይ ብቻ እንዳያተኩሩ አሳስበዋል።

እነዚህ ንግግሮች በቻይና–አፍሪካ የአፍሪካ ሀገራት ከቻይና የመሳሰሉ አጋሮች ጋር በታዳሽ ኃይል፣ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪዎች እና የአየር ንብረትን የሚቋቋም ልማት ላይ ለመስራት ያላትን ራዕይ ያንፀባርቃሉ።

ቻይና የአፍሪካ ሀገራትን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ጥረት ወሳኝ ሚና እየተጫወተች ነች። በታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በፎካክ ማዕቀፍ ውስጥ በሚካሄድ የስትራቴጂ ፖሊሲ ትብብር፣ ሁለቱም ወገኖች አፍሪካ ወደ ዝቅተኛ የካርቦን ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።
የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ “ቻይናና አፍሪካ ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛውን ይይዛሉ። የእኛ ዘመናዊነት ካልተሳካ የዓለም ዘመናዊነት አይሳካም” ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ንግግር በአፍሪካ የሚከናወነው የተሳካ የአየር ንብረት እርምጃ፣ በዓለም አቀፍ አጋርነት ሲደገፍ፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካትና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የጋራ ፈተና ለመፍታት ያስችላል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው