Loading...

የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ቃልኪዳኖች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ጥሪ በማቅረብ ተጠናቀቀ

Africa Ends Climate Conference with Call to Turn Pledges Into Action

ለበርካታ አመታት የተገቡ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖች በአብዛኛው ተግባራዊ ሳይደረጉ በመቆየታቸው፣ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች አገልግሎት ሳያገኙ ቆይተዋል።

በአዲስ አበባ ለሦስት ቀናት የተካሄደውን የአፍሪካ 14ኛው የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ (CCDA-14) ያጠናቀቁት የአፍሪካ የአየር ንብረት ባለድርሻዎች አንድ ግልጽ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ ጊዜው ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባር የሚቀየሩበት ነው የሚል ነው

ጉባኤው ረቡዕ ዕለት ሲጠናቀቅ፣ አፍሪካ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት አጀንዳ ቅርጽ በመስጠት ረገድ የበለጠ ተሳትፎና ተፅዕኖ እንዲኖራት እንዲሁም አህጉሪቱ በአንፃራዊነት በችግሩ መፈጠር ላይ አነስተኛ ድርሻ ቢኖራትም የሚገጥማትን ቀውስ ለመቋቋም የሚረዳት የታመነና ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዲገኝ ጠይቋል

“ከቃል ኪዳን ወደ ተግባር፡ የቤሌም–አንታሊያ–አዲስ አበባ የጉዞ ካርታ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ጉባኤ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የአየር ንብረት ድርድር ተደራዳሪዎችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ተመራማሪዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖችን፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችንና የግሉ ዘርፍ ተወካዮችን አሰባስቧል።
ውይይቶቹ የጀመሩት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በተሰጡ ቃል ኪዳኖችና በተግባራዊ እርምጃዎች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መምጣቱን በመግለጽ ነበር።

በመጨረሻ ግን ተሳታፊዎቹ ሰፋ ያለ ራዕይ አስቀምጠዋል፤ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት የሚደርስባት ብቻ ሳትሆን፣ መፍትሄዎችን ማበርከትና በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፖሊሲ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር የምትችል አህጉር መሆን እንዳለባት ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ምክትል ዋና ጸሐፊ ሃናን ሞርሲ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ እንደተናገሩት የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ በፍትሃዊነት፣ በዘላቂ ልማት፣ በተጠያቂነትና በአፍሪካዊ ባለቤትነት ላይ መመስረት አለበት።
ጉባኤው አፍሪካ በአንታሊያ ለሚካሄደው ለ31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ (COP31) እና በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ለ32ኛው ጉባኤ (COP32) በቃልኪዳኖች ተግባራዊነት ላይ እንድታተኩር ጠይቋል።
በተለይም ተገማች፣ ተደራሽና በእዳ የማይጭን የአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲገኝ ጥሪ አቅርቧል።

የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖች

የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖችን በመግባት ችግር ባይኖርም፣ አፈጻጸሙ መገምገም ግን እጅግ ኋላ መቅረቱን ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

ጉባኤው ሲከፈት የኢሲኤ ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በስብሰባው ውስጥ በተደጋጋሚ የተነሳውን ብስጭት በግልጽ ቃላት ገልጸው ነበር።
“ብዙ ቃል ኪዳኖችን ተደራድረናል። ግቦችን አስቀምጠናል። በብሔራዊ ደረጃ የሚወሰኑ የአየር ንብረት አስተዋጽኦዎችን (NDCs) እና ብሔራዊ የማላመድ ዕቅዶችን አዘጋጅተናል። ሆኖም ትግበራው አሁንም ኋላ ቀርቷል።” ብለዋል።
ለብዙ ተሳታፊዎች፣ በቃል ኪዳንና በተግባር መካከል ያለው ክፍተት ከእንግዲህ በቀላሉ ሊታለፍ የማይችል ጉዳይ ሆኗል።
የፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትህ ህብረት (PACJA) ዋና ዳይሬክተር ሚቲካ መዌንዳም በቀደሙት የአየር ንብረት ጉባኤዎች የተሰጡት ቃል ኪዳኖች በእርግጥ ወደ አፍሪካ እየደረሱ መሆናቸውን ጠይቀዋል።
መዌንዳ ለአፍሮ-ኢንሳይት በሰጡት አስተያየት፣ “መግለጫዎችንና ቃል ኪዳኖችን በመስጠት በጣም ጥሩ ነን። ነገር ግን ወደ ትግበራ ሲመጣ ነው ችግሩ ያለው።” ብለዋል።

ጉባኤው ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች ትግበራው በተጨባጭ መለካት እንዳለበት ጠይቀዋል። ይህም በአዳዲስ መግለጫዎች ብቻ ሳይሆን፣ በሕጎች፣ በብሔራዊ በጀቶች፣ በኢንቨስትመንቶች፣ በሚሰሩ ተቋማትና ሕዝብ ሊያየው በሚችለው ውጤት መመዘን አለበት ብለዋል።
የአፍሪካ ፓርላማዎችም ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖችን ወደ ብሔራዊ ሕጎች፣ በጀቶችና የክትትል ሥርዓቶች በመቀየር ረገድ የበለጠ ሚና እንዲወጡ ተጠይቀዋል።

የአየር ንብረት ፋይናንስ

የአፍሪካ ትልቁ ጥያቄ አሁንም የአየር ንብረት ፋይናንስ ነው፤ የውይይቱ ዋና አጀንዳም ነበር።
አፍሪካ ከዓለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ከ4 በመቶ በታች የምታዋጣ ቢሆንም፣ የአህጉሪቱን የአየር ንብረት ዕቅዶች እስከ 2030 ለመተግበር በየዓመቱ ወደ 277 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል። አሁን የሚገኘው የአየር ንብረት ፋይናንስ የዚህን ፍላጎት 11 በመቶ ያህል ብቻ ይሸፍናል።
ተሳታፊዎች ይህ ክፍተት በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ምላሽ  ውስጥ ያለውን አለመመጣጠን በግልጽ የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብለዋል።
መዌንዳ በባኩ፣ አዘርባጃን በተካሄደው COP29 የተደረሱ የፋይናንስ ቃል ኪዳኖችን በመጥቀስ፣ በየዓመቱ 300 ቢሊዮን ዶላር የአየር ንብረት ፋይናንስ ለማቅረብና እስከ 2035 ድረስ ይህንን ፋይናንስ ወደ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ለማሳደግ የተያዘውን ምኞት አስታውሰዋል።
ጥያቄው ግን እነዚህ ቃል ኪዳኖች በእርግጥ ይፈጸማሉ ወይ? የሚለው ነው ይላሉ።
ጉባኤው የበለጸጉ ሀገራት የአየር ንብረት ፋይናንስ ግዴታዎቻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። በተጨማሪም የአፍሪካ አገራትን በበለጠ ዕዳ ውስጥ የሚከቱ የፋይናንስ አሰጣጥ ሞዴሎች እንዲቀየሩ ጠይቋል።
ተሳታፊዎች የአየር ንብረት ፋይናንስ የተናጠል ፕሮጀክቶችን ከመደገፍ በላይ ሊሠራ ይገባል ብለዋል። ፋይናንሱ የአፍሪካ ኢኮኖሚዎች ሥራ እንዲፈጥሩ፣ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያሳድጉ፣ ቴክኖሎጂ እንዲያስተላልፉና ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ እሴት በአፍሪካ ውስጥ እንዲቀር ማገዝ አለበት።
ተሳታፊዎች የአየር ንብረት ለውጥን መላመድም (adaptation ) እንደ ወጪ ሳይሆን እንደ ኢንቨስትመንት መታየት አለበት ብለዋል።
በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማትም በኩል የለውጥ ምልክቶች ታይተዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ የመላመድ ማፋጠኛ ፕሮግራም ስር ከ25 ቢሊዮን ዶላር ግቡ ውስጥ 19 ቢሊዮን ዶላር፣ ወይም 78 በመቶ፣ ማሰባሰቡን ገልጿል።
የአፍሪካ ኤክስፖርት–ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) ደግሞ እስከ 2030 ድረስ ከረጅም ጊዜ ብድሮቹ 5 በመቶውን ለአየር ንብረት ፋይናንስ ለመመደብ ዕቅድ እንዳለው ገልጿል። ከዚህ ፋይናንስ ውስጥ 70 በመቶው ለመላመድ እንደሚውልም አስታውቋል።

ከተጋላጭነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት

ከጉባኤው የወጡ ጠንካራ መልዕክቶች አንዱ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች ላይ የምትከተለውን አቀራረብ መቀየር እንደምትፈልግ ነው።
የኢሲኤ ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፣ የአፍሪካ የአየር ንብረት ታሪክ በተጋላጭነት ብቻ መገለጽ እንደሌለበት ተናግረዋል። አህጉሪቱ ለአየር ንብረት ፍትሕና ለበለጠ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ጥረት እያደረገች፣ የራሷን ሀብቶችና አቅሞች በተሻለ ሁኔታ መጠቀም እንዳለባት ጠይቀዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ጥያቄው ከእንግዲህ በCOP31 ላይ አፍሪካ ምን መጠየቅ አለባት ብቻ ሳይሆን፣ አፍሪካ ለዓለም ምን ማቅረብ ትችላለች? መሆን አለበት ብለዋል።ይህንን ሀሳብ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካይ ጄምስ ኪንያንጊም ደግፈዋል።
“አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጎጂ ብቻ አይደለችም። የመፍትሄዎች ምንጭ ነን።” ብለዋል።
የAfreximbank ተወካይ ኦሉቡንሚ ኦባሶንጆ–ዊሊያምስም የአፍሪካን የአየር ንብረት ታሪክ በተጋላጭነት ብቻ መወሰን እንደሌለበት አሳስበዋል።

ወሳኝ ማዕድናት

ጉባኤው በአፍሪካ ወሳኝ የማዕድናት ክምችት ላይም ትኩረት አድርጓል። እነዚህ ማዕድናት ዓለም ወደ ንጹህ ኃይል ለሚያደርገው ሽግግር እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
ተሳታፊዎች የኃይል ሽግግሩ አፍሪካ ጥሬ ማዕድናትን ወደ ውጭ ልካ ከፍተኛ እሴት ያላቸውን ቴክኖሎጂዎችና ምርቶች እንድታስገባ የሚያደርግ መሆን የለበትም ብለዋል።
በምትኩ፣ ማዕድን አምራች ሀገራት በአካባቢያዊ ማቀነባበርና ማምረት ተጨማሪ ዋጋውን በራሳቸው ማስቀረት፣ ሥራ መፍጠርና የአፍሪካን ኢንዱስትሪ ማጠናከር አለባቸው ተብሏል።
ተሳታፊዎች ከአፍሪካ የማዕድን ራዕይ፣ ከአፍሪካ አረንጓዴ ማዕድናት ስትራቴጂ እና ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር የተጣጣመ ጠንካራ የክልል ትብብር እንዲኖር ጠይቀዋል።
መልዕክቱም ግልጽ ነበር፤ ፍትሃዊ የኃይል ሽግግር ማለት ፍትሃዊ የማዕድናት ሽግግርም ማለት ነው።
ኪንያንጊ አፍሪካ ከዓለም የፀሐይ ኃይል አቅም 60 በመቶ ያህል እንዳላት ገልጸዋል። ኦባሶንጆ–ዊሊያምስ ደግሞ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክና የዛምቢያ 3 ቢሊዮን ዶላር የባትሪ የእሴት ሰንሰለት ፕሮጀክት የአፍሪካን የማዕድን ሀብት ከኢንዱስትሪ ልማት ጋር ለማስተሳሰር ምሳሌ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የአየር ንብረት እሮምጃ ለማህበረሰቦች

ጉባኤው ከዓለም አቀፍ ድርድሮች ባሻገር በየዕለቱ በሕዝብ ላይ የሚታዩትን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችም ተመልክቷል። ተሳታፊዎች ለተላጭ ማህበረሰቦች፣ ከተሞችና የአካባቢው መንግስታት ጠንካራ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች፣ የተሻለ የአየር ንብረት መረጃና ለመላመድ የሚረዳ  ኢንቨስትመንት እንዲኖር ጠይቀዋል።

የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ጎርፍ፣ ድርቅ ወይም ከፍተኛ የአየር ሁኔታ ክስተት እንደሚከሰት መተንበይ ላይ ብቻ ሊቆም እንደሌለበት ተገልጿል። መረጃው በበቂ ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ መድረስና ከፋይናንስና ተግባራዊ ምላሽ ጋር መገናኘት አለበት።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው