Loading...

ከኢቦላ ባሻገር፡ የቻይና እና የአፍሪካ ትብብር የአፍሪካን የጤና ደህንነት እንዴት እየቀረጸው ነው?

Beyond Ebola: How China-Africa cooperation is reshaping Africa’s health security

በኢትዮጵያ ካለው ትልቅ የጤና ህንጻ እስከ መካከለኛው አፍሪካ የጸረ-ኢቦላ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ድረስ ቻይና እና አፍሪካ፣ የአህጉሪቱ የጤና ችግሮች እየጨመሩ ባለበት በዚህ ወቅት ትብብራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ይህ ጥምረት በታሪክ ትልቅ የተባለውን የኢቦላ ወረረሽኝ እየተዋጋች ላለችው ኮንጎ ጠቀሜታው የጎላ ነው።

የኮንጎ የጤና ሚንስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዶር ብሩኖ ቢንዳምባ ለአፍሮ ኢንሳይት እንደተናገሩት እኤአ እስከ ነሐሴ 26, 2026 ድረስ፣ ቡንዲቡግዮ በተባለው የኢቦላ ቫይረስ ምክንያት ከ 2000 በላይ የሆኑ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 6000 የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ፎቶ፡ ዶ/ር ብሩኖ ቢንዳምባ ሰንጌ
የብሔራዊ ሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ፣ ዲ አር ሲ

ቫይረስ በበርካታ ግዛቶች በመዛመቱ ምክንያት ደካማ በሆነው የጤና ስርአት ላይ ከባድ ጫና ከማሳደሩ በተጨማሪ ወደ ሌሎች ቀጠናዎች ይስፋፋል የሚል ስጋትም ደቅኗል። ይህ ቀውሰ የአፍሪካ ሀገራት ጠንካራ የበሽታ መከላከያ ስርአት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ስርአት እንዲሁም ለድንገተኛ አደጋዎችን ምላሽ የሚሰጥ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልገው ጠቋሚ  ነው። ለዚህ ነው እያደገ የመጣው የቻይና-አፍሪካ ትብብር አስፈላጊ የሚሆነው።

ከመሰረተ ልማት እስከ ጤና ሴኩሪቲ

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል(Africa Centers for Disease Control and Prevention-CDC ) ህንጻ ግንባታ ቻይና በጤናው ዘርፍ ለአፍሪካ የምታደርገው ድጋፍ ዋነኛ ማሳያ ነው። ማዕከሉ ለአህጉር አቀፍ የበሽታ መከላከል፣ የአደጋ ጊዜ ዝግጅትና ለቅንጅት እንደማስተባበሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ትብብሩ ከግንባታና ከመሳሪያ እርዳታ በላይ እየሆነ ነው።

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል(ሲዲሲ) እና የቻይና የጤና ተቋማት በበሽታ ክትትል፣በላቦራቶሪ አቅም ግንባታ፣ በቀዶ ጥገና፣ በስልጠና በወረርሽኝ ምላሽ እና በሌሎችም ጉዳዮች በትብብር እየሰሩ ናቸው። የትብብሩ አላማ በሽታው አህጉር አቀፍ ከመሆኑ በፊት የአፍሪካ ሀገራት የመመርመርንና ምላሽ የመስጠት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ማስቻል ነው።

በኢቦላ የተፈተነው ትብብር

በአሁኑ ወቅት በኮንጎ የተከሰተው ወረርሽኝ ትብብሩ እንዲፈተን አድርጎታል። ባለፈው ሰኔ ወር ቻይና፣ አፍሪካ ለወረርሽኙ የምትሰጠውን ምላሽ አቅም ለማሳደግ ሰብአዊ ድጋፍ አድርጋለች።በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ጂያንግ ፌንግ እና የአፍሪካ ሲዲሲ ዳይሬክተር ዶክተር ጂን ካሰያ የድጋፉን ርክክብ ተፈራርመዋል።

ካሰያ የቻይና ድጋፍ አህጉሪቱ ለምታደርገው ምላሽ ጠቃሚ መሆኑንና ሲዲስ ከቻይና ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት ገልጸው ነበር።

የኢቦላ ቀውስ ቅድመ ዝግጅት አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የአሁኑን ወረረሽኝ ያስከተለው የቡድንዲቡግዮ ቫይረስ የተረጋገጠ ክትባት ስለሌለው የምላሽ ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል። ከምርምር ጎን ለጎን  የጤና ባለስልጣናት ወረርሽኙን የመቆጣጠር የመከታተል፣ የመለየት፣ የንክኪ መነሻ ፍለጋ፣ ኢንፌክሽን የመከላከል፣ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን የአለምጤና ድርጅት አስታውቋል። ለአፍሪካ ሲዲሲ ከባድ የሆነው ለአሁኑ ወረርሽን ምላሽ የመስጠት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ሊመጣ ለሚችል ወረርሽን ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ነው።

ከኢቦላ ባሻገር

ኢቦላ ከሰፊው የጤና አጀንዳ አንዱ ነው። በመላው አፍሪካ መንግስታትና የጤና ተቋማት የወባ በሽታን፣ ኤችአይቪን፣ ሳምባ ነቀርሳንና ሌሎች በሽታዎችን እየተከላከሉ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን በድንገት ለሚከሰቱ ወረርሽኞችም እየተዘጋጁ ነው። ይህ በላቦራቶሪ፣በሳይንሳዊ ጥናትና በጤና ባለሙያዎች ዘርፉ ያለውን ትብብር የበለጠ አስፈላጊ ያደርገዋል። ለቻይና ከአፍሪካ የጤና ተቋማት ጋር የምታደርገው ትብብር የሰፊው የህብረተሰብ ጤና ትብብር አካል ነው።  ለአፍሪካ ግን የአቅምና የባለቤትነት ጉዳይ ነው። አለምአቀፍ ትብብር የአፍሪካ ሀገራትን የራሳቸውን ምላሽ የመስጠት፣ የመመርመርና የራሳቸውን መፍትሔ የመቅረብ አቅም እንዴት ያሳድግላቸዋል የሚለው ቁልፍ የሚለው ነው ወሳኙ ነጥብ።

የአፍሪካን አቅም መገንባት

የአፍሪካን አቅም የመገንባት ጉዳይ በተለይ በአፍሪካ ሲዲሲ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ አስፈላጊ መወያያ ርዕስ ነው። የአፍሪካ ሳይንቲስቶች በአህጉሪቱ በሚገኙ የጤና ላቦራቶሪዎችና የህብረተሰብ ጤና ተቋማት በበሽታ ምርመራ፣በዘረመል ክትትል፣በቀዶ ጥገናና በወረርሽኝ ዝግጁነት ላይ እየሰሩ ናቸው። የረጅም ጊዜ አላማውም ወረርሽኝ ሲከሰት ምላሽ መስጠት ብቻ አይደለም። በሽታ ሲከሰት ቀድሞ ለማወቅ፣ ፓቶጅን ለመለየት፣ መረጃን በፍጥነት ለመለዋወጥና ድንበር ዘለል ትብብሮችን ለማቀናጀት ነው። የኢቦላ ወረርሽኝ እንዲህ አይነት ትብብር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክታል። ይህ ወረርሽኝ  ባለመረጋጋትና በህዝብ ፍልሰት ምክንያት የጤና ተቋማት ተደራሽነት አስቸጋሪ በሆነበት ቀጠና በመሆኑ ወረርሽኙን የመከላከልን ጥረት ፈታኝ አድርጎታል

ለቀጣይ ወረርሽኝ የሚደረግ ትብብር

የቻይና አፍሪካ የጤና ዘርፍ ትብብር ለአንድ ወረርሽኝ ምላሽ ከመስጠት የተሻገረ ፈተና አጋጥሞታል። የትብብሩ ውጤታማነትም የሚለካው ከፍተኛ የጤና ሴኩሪቲ በማሳደግ ነው የሚሆነው

የበሽታ ቁጥጥር፣ የድንገተኛ ዝግጁነትና በመላ አህጉሪቱ ምላሽ መስጠትን ያካተት ተልእኮ ላለው የአፍሪካ ሲዲሲ፣ ትብብሩ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ገልጿል። ይህ ደግሞ ጠንካራ የአፍሪካ ተቋማትን፣ሳይንሳዊ አቅምና ትብብር  አፍሪካ ቀጣይ ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት እንድትዘጋጅ ይረዳታል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው