Loading...

ብሔራዊ ባንክ በዓመታዊ የብድር ገደብ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ማንሳቱን አስታወቀ

ብሔራዊ ባንክ በዓመታዊ የብድር ገደብ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ማንሳቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትናንት ባወጣው መግለጫ ንግድ ባንኮች በሚያበድሩት አመታዊ የብድር መጠን ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ማንሳቱን አስታውቋል

ባንኩ የተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን በገመገመበት በዚህ መግለጫው በጊዚያዊነት ሲጠቀምበት የነበረው የብድር ገደብ ፖሊሲ አላማውን በማሳካቱ  ሙሉ በሙሉ ተነስቷል ብሏል። ውሳኔው የባንኩ “ጥብቅ የፖሊሲ ለውጥ አቋም” አለመሆኑንና ቅደመ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሷል ባንኩ።

ባንኩ “ይህ የብድር ገደብ መነሳት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የፖሊሲ አቋም ለውጥ ሳይሆን የወለድ ተመንን መሰረት ያደረገው የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ወደ ተሳካ ሽግግር በመድረሱና ቀጥተኛ ያልሆኑ የገንዘብ ፖሊሲ መሳሪያዎች ውጤታማ እየሆኑ በማጣታቸው ነው” ብሏል

ባንኩ እንደገለጸው የብድር ገደቡ ቢነሳም ተመጣጣኝ የሆነ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ለማስቀጠል ቀጥተኛ ያልሆኑ የገንዘብ መሳሪያዎች መጠቀሙን ይቀጥልበታል።

ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔን በ1.0በመቶኛ  (ከ15 ወደ 16 በመቶ) እንዲያድግ ይደረጋል ያለው ባንኩ  የብድር እድገት የዋጋ ግሽበት በሚያስከትልበት ወቅት በእያንዳንዱ ባንክ የብድርና ተቀማጭ ምጥነት ላይ በመመርኮዝ የተለየ የመጠባበቂያ ተቀማጭ እንዲተግብር እንደሚደረግም ጠቅሷል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሬ ኮሚሽን ምጣኔ ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ እንዲቀንስ እንዲሁም ላኪዎች ከውጭ ምንዛሬ ግኝታቸው ላይ ለባንኮች እንዲሸጡ የሚገደዱት 50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ወስኗል። ባንኩ ይህን ያደረገው የዋጋ ግሽበት ተጽዕኖ ለመቀነስና የውጭ ንግድ ተወዳዳሪነት ለማሻሻል መሆኑን ገልጿል።

ባንኩ የአሜሪካ ኢራን ጦርነት በታህሳስ 2018 መቀስቀሱን ተከትሎ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሀዝ መመለሱን፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት ባለፉት ስምምነት አመታት ከተመዘገበው 7.5 በመቶ ወደ 9.2በመቶ ማደጉንና የመንግስት የግምዣ ቤት ሰነድ ወለድ መቀኑሱን መገምገሙን ጠቅሏል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው