ለንግድ ድርጅትዎ የእቃ ግብይት በግል ሂሳብዎ ተጠቅመዋል? አዲሱን የብሔራዊ ባንክ ማሳሰቢያ ይመልከቱ
የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች፥ ለንግድ ስራቸው ተብሎ ከተከፈተው ውጪ በግል የባንክ ሂሳባቸው ወይም የሶስተኛ ወገን ሂሳብ ተጠቅመው ግብይት እያካሄዱ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ በማለት ብሄራዊ ባንክ ገልጿል። ይህ አሰራር ከግብር ለማምለጥ የሚደረግ ጥረት ሲሆን ወንጀል ከመሆኑም በላይ ሽብርተኝነትን ለመደገፍ ሊውል ስለሚችል እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አሳስቧል። ባንኮችም ህጋዊ እና ህገ-ወጥ ደንበኞቹን አጥርተው እንዲለዩ እና መረጃዎቹን እንዲልኩ ጠይቋል።














