Loading...

ኢትዮጵያ በታይዋን ጉዳይ ላይ ለቻይና ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ አረጋገጠች

Chairperson of the Foreign Relations and Peace Affairs Standing Committee at Ethiopia’s House of Peoples’ Representatives (HoPR), Dr. Dima Negewo, has reaffirmed Ethiopia’s strong support for China regarding Taiwan.

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ከአፍሮ ኢንሳይነት ጋር ባደረጉት ልዩ ቃለምልልስ ኢትዮጵያ በታይዋን ጉዳይ ላይ ለቻይና ያላትን ጠንካራ ድጋፍ እንደምታስቀጥል አረጋግጠዋል።

ዶ/ር ዲማ ይህን ያረጋገጡት የታይዋን ክልል መሪ ቺንግ-ቴ በቅርቡ የታይዋንን ነፃነት የሚደግፍ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

ዶ/ር ዲማ ኢትዮጵያ ታይዋንን በተመለከተ ያላት አቋም መንግስት ሲቀያየር የማይቀየር ነው ብለዋል። እአአ በ1971 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የታይዋንን ወኪልነት በማስወገድ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክን የቻይና ሕጋዊ ተወካይ አድርጎ ሲመርጥ ኢትዮጵያ ድጋፋቸውን ከሰጡት የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ እንደነበረች ዶ/ር ዲማ አስታውሰዋል።
“የኢትዮጵያ አቋም የማይናወጥ ነው፤ በጣም ግልጽም ነው” ሲሉ ዶ/ር ዲማ ተናግረዋል።
“በተለያዩ ሥርዓቶችና መንግሥታት ዘመን ሁሉ የኢትዮጵያ አቋም አንድ ነው። የቻይናን አንድነት እንደግፋለን፤ ታይዋንም የቻይና ዋና አካል መሆኗን እናምናለን። የታይዋን ጉዳይ የቻይ ውስጣዊ ጉዳይ ነው፤ በዋናው ምድርና (mainland China) እና በደሴቱ(Taiwan) መካከል ያሉ ልዩነቶችን መፍታት የቻይና ሕዝብ ጉዳይ ነው”።

ቺንግ-ቴ ስላደረጉት ንግግር የተጠየቁት ዶ/ር ዲማ እነዚህ አስተያየቶች በዋናነት ለውስጣዊ ፖለቲካ ፍጆታ የተደረጉ ናቸው ሲሉ አጣጥለዋል።

ዶ/ር ዲማ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም “ታይዋን የቻይና ክፍለ ግዛት ናት፤ ወደ ቻይናም መመለስ አለባት” የሚል መሆኑን ገልጸዋል።እሳቸው እንደሚሉት አሜሪካ በተለይም ከመሣሪያ ሽያጭ ስምምነቶች ጋር ተያይዞ እየሰጠች ያለው ድጋፍ፣ አሁን ያለው የታይዋን አመራር ድፍረት እንዲያገኝ አድርጎታል።

የኢትዮጵያ–ቻይና ሁለትዮሽ ግንኙነት

ዶ/ር ዲማ ለስድስት አስርት ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያና የቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት፣ ቻይና በባቡር፣ በመንገድ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በሌሎች መሠረተ ልማት ዘርፎች እያደረገች ባለው ኢንቨስትመንት  እየጠነከረ መሆኑን ተናግረዋል። 

እንደ ዶ/ር ዲማ ገለጻ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የቻይና ኢንቨስትመንት 5 ቢሊዮን ዶላር ያህል ሲሆን፣ በቻይና ባለቤትነት የሚተዳደሩ ኢንዱስትሪዎች ለ65,000 ገደማ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል ፈጥረዋል

ዶ/ር ዲማ እንደገለጹት የሁለቱ ሀገራት  ፓርላማዎች የሚያደርጉት ውይይት የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ እንዲጠናከር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው። በቅርቡ በቻይና ብሔራዊ የሕዝብ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ግብዣ ወደ ቻይና ተጉዘው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ዲማ የኮሚቴው ሰብሳቢ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ግብዣ ተደርጎላቸዋል ብለዋል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው