Afro-Insight News – ሃሪኬን ሜሊሳ የተባለ ከባድ አውሎንፋስ ጃማይካ ውስጥ የምትገኝ የደሴት ከተማን አውድሟል። በጃማይካ እና ሃይቲ ውስጥ በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 49 የደረሰ ሲሆን በሺህ የቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረት አልባ ሆነዋል። ደሴቷ በከባድ ንፋስ እና ዝናብ ተጥለቅልቃለች:: የተጎዱ ህንጻዎች ፣ ጣራቸው የፈራረሱ መኖሪያዎች እና በግማሽ የቆሙ ግድግዳዎች ብቻ ይታያሉ።
አውሎንፋሱ ኩባ ላይም የደረሰ ሲሆን አደጋው ከመድረሱ አስቀድሞ በተሰጠ ማስጠንቀቂያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አከባቢያቸውን ጥለው እንዲሸሹ ተደርገዋል። አሜሪካ ለኩባ ድጋፍ ለማቅረብ ዝግጁ ነኝ ያለች ሲሆን ሁለቱ አገራት ያላቸው የባላንጣነት ታሪክ እና የስድሳ አመታት ማዕቀብ እንዳለ ነው።
አውሎ ንፋሱ ከ170 አመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ፥ እጅግ ሃይለኛ እንደሆነ ተገልጿል።











