የአሜሪካ ጦር ዲፓርትመንት ዋና አዛዥ የጦር ወንጀል ፈጽሟል በሚል ምርመራ ተከፍቶበታል።
በጦር አዛዡ ፒት ሄግዚት በተሰጠ ትዕዛዝ፥ በእጽ አዘዋዋሪ ናቸው በሚል የተጠረጠሩ ሃያ ሁለት ጀልባዎች ላይ በዚህ ሳምንት የተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ሰማንያ ሰዎች ተገድለው ነበር።
አዲሱ ውንጀላ የመጣው፥ በዚያ ጥቃት ላይ ከመጀመሪያ ዙር የቦምብ ጥቃት መትረፍ የቻሉ እና ነፍሳቸውን ለማዳን ጀልባ ላይ ተንጠላጥለው የነበሩ ሁለት ሰዎች ላይ ሁለተኛ ዙር የቦምብ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ትዕዛዝ በመሰጠቱ እንደነበር ተገልጿል። ይህ ጥቃት የጦር ህጎችን የጣሰ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪ የአሜሪካ ጦር አዛዦች ከዚህ ጥቃት ጋር በተያየዘ ሌሎች ክሶችም ሊቀርብባቸው እንደሚችል የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ያስረዳል።
ዋይትሃውስ፥ ሁለተኛ ዙር ጥቃት መፈጸሙን አምኖ፥ ጥቃቱ የባህር ሃይል አድሚራሉ ፍራንክ ብራድሊ ህጋዊ ስልጣኑን ተጠቅሞ በሰጠው ውሳኔ እንደተፈጸመ ገልጿል።
የእጽ አዘዋዋሪ ጀልባዎቹ የቬንዙዌላ ንብረቶች ሲሆኑ፥ በጀልባዎቹ ላይ የተሰነዘረው የአየር ጥቃት፥ ዶናልድ ትራምፕ የኒኮላስ ማዱሮ መንግስት ላይ የከፈቱት ዘመቻ አካል ተደርጎ ተቆጥሯል።
ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት ነው።












