Loading...

ሩዋንዳና ኮንጎ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

ሩዋንዳና እና ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ(ዲ.አር.ሲ.) በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተናጋጅነት በምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየውን ግጭት ለማስቆሞ ያለመ የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዮሱፍ ይህ ስምምነቱ በትልቁ ሀይቅ ቀጠና(ግሬት ሌክ ሪጅን) ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር መሰረት የሚሆን ነው ሲሉ አድንቀውታል።

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በሩዋንዳ መንግስት ይደገፋሉ የሚባሉት የኤም-23 አማጺያን በምስራቅ ኮንጎ መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት የግዛቱን ሁለት ትልልቅ ከተሞች ተቆጣጥረዋል። ይህ በሽዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን እንዲገደሉና ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።

የስምምነቱን ሂደት የመሩት ትራምፕ ከፊርማ ስነስርዓቱ በፊት ይህ ለአፍሪካና ለሌላው አለም “ትልቅ ቀን” ነው ሱሉ ተናግረዋል።
በሁለቱም መሪዎች እምነት አለኝ” ያሉት ትራምፕ “መሪዎቹ ቃላቸውን በመጠበቅ ለህዝባቸው ብርህ የሆነ መፃኢ እድል እንደሚፈጥሩ አቃለሁ” ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪትም ትራምፕ በምስራቅ ኮንጎ ያለውን ብርቅ ማዕድናት የአሜሪካ ኩባንያዎች በሚያወጡበት ሁኔታ ከመሪዎቹ ጋር የሁለት ስምምነት መፈራረማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የዲ.አር.ሲ. ፕሬዝደንት ፍሌክሲ ቲሽስኬዲ እና የሩዋንዳው አቻቸው ፖል ካጋሜ በተደጋጋሚ ይሰዳደባሉ፤ ግጭቱን በመጀመርም አንዳቸው ሌላኛቸውን ሲከሱ ይደመጣሉ።


ትራምፕ የሁለቱን ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ሀምሌ ወር ስምምነት ሲፈራረሙ አግኝተዋቸው የነበረ ሲሆን ስምምነቱን “ትልቅ ድል” በማለት ነበር የገጹት።
ትሽስኬዲ እና ካጋሜ ይህን ስምምነት አሁን ላይ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በታዛቢነት በተገኙት የዋሽንግተኑ ስነስርዓት አጽድቀውታል።
ትራምፕን “በፍጹም ወደ አንድ ወገን የማያዳላ” ሲሉ የገለጹት ካጋሜ ይህ አካሄድ ከዚህ በፊት ከበሩት ሁሉ ግልጽና የሚሳካ ነው ብለዋል።
ትሽስኬዲም እንዲሁ “ክብርና ተስፋ” እንዳቸው ገልጸው፣ ሩዋንዳ ስምምነቱን ታከብራለች የሚል ተስፋ አላቸው። በስምምነቱ ላይ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በተጨማሪ የኳታርና የአረብ ኤምሬትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

የምስራቃዊ ኮንጎ ግጭት መነሻ

በምስራቃዊ ኮንጎ ያለው ግጭት የተነሳው እ.ኤ.አ. በ1994 በሩዋንዳ የሁቱ ጎሳ ታጣቂዎች አንድ ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ የቱትሲ ጎሳ አባላትን፣ ለዘብተኛ ሁቱዎችንና ትዋ የተባሉ ነባር ህዝቦችን ከገደሉ በኋላ ነበር።

በቱትሲ የሚመራው ኃይል ባደረገው ማጥቃት በቀልን የፈሩ 2 ሚሊዮን ገደማ ሁቱዎች ድንበር አቋርጠው ኮንጎ ለመግባት ተገደዱ። ሩዋንዳ እነዚህን የተሰደዱ ሁቱዎች በዘር ማጥፋት የተሳተፉ መሆናቸውንና የኮንጎ ጦር ክፍል ከለላ እየሰጣቸው እንደሆነ ትከሳለች። በሁቱዎች የተደራጀው ሚሊሻ ለዋሩንዳ ቱትሲ ህዝብ አደጋ መደቀኑን ትገልጻለች።

ኮንጎ በአንጻሩ ይህን ክስ በማስተባበል የሩዋንዳ ጦር ከግዟታ ለቆ የማይወጣ ከሆነ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንደሚያስቸግር ስትገልጽ ቆይታለች።

Share this article

One Response

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው