Loading...

አሜሪካ፥ ለኬንያ የጤና ዘርፍ የሚውል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አቅርባለች

በአሜሪካ ሴክሬተሪ ኦፍ ስቴት ማርኮ ሩቢዮ እና የኬንያ ፕራይም ካቢኔ ጸሃፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ የተፈረመው ስምምነት በትራምፕ አስተዳደር የውጭ እርዳታ ማሻሻያ ከተደረገ በሗላ የተፈጸመ የመጀመሪያው አለም አቀፍ ድጋፍ እንደሆነ ተገልጿል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ፥ ስምምነቱ ኬንያ በቀጣዮቹ አምስት አማታት በእራሷ የጤና ዘርፍ በጀቷን በ850 ሚሊዮን ዶላር እንድታሳድግ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ ነበር። ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በሚቀጥሉት ቀናት ተመሳሳይ ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙ የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

አሜሪካ በአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር መስከረም ወር ላይ “አሜሪካ ፈርስት አለም አቀፍ የጤና ስትራቴጂ” በሚል ይፋ ያደረገችው የድጋፍ ማዕቀፍ፥ ድሃ አገራት ኤችአይቪ/ኤድስ፣ ወባ፣ ሳንባ ነቀርሳ እና ፖሊዮን በመዋጋት ረገድ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ እና በመጨረሻም ከእርዳታ እራስችን ወደመቻል እንዲሸጋገሩ ለማገዝ የተቀረጸ፥ አዲሱ የአሜሪካ አለም አቀፍ የድጋፍ ፖሊሲ አካል እንደሆነ ሮይተርስ በዘገባው ገልጿል።

የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዊሊያም ሩቶ፥ ስምምነቱ ለኬንያ የጤና ዘርፍ ትልቅ እድገት የሚያመጣ እንደሆነ ገልጸዋል። ድጋፉ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን ለሆስፒታሎች ለማቅረብ ፣አስፈላጊ የጤና አገልግሎት ቁሳቁሶችን በወቅቱ ለጤና ተቋማት ለማድረስ ፣የጤና ሰራተኞችን አቅም ለማሻሻል እና የጤና መድህን ለማስፋፋት እንደሚውል ሩቶ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው