Loading...

የቤኒን መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማክሸፉን ገልጿል

የቤኒን ወታደሮች በመንግስት የቴሌቭዥን ጣብያ ላይ ቀርበው መፈንቅለ መንግስት ማካሄዳቸውን ከተነጋሩ ከሰዓታት በሗላ መንግስት ሙከራው መክሸፉን ገልጿል። የቤኒን ባለሥልጣናት የመንግስት ሃይሎች ሙከራውን እንዳከሸፉ እና የፕሬዝደንቱ ፓትሪስ ታሎን ደህነነት አረጋግጠዋል።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አላሳኔ ሴይዱ በኋላ በቪዲዮ መግለጫ “ድርጊቱን የፈጸሙት ወታደሮች መንግስት እና ተቋማቱ ላይ አለመረጋጋትን ለመፍጠር እና ሰላምን ለማደፍረስ ያሰቡ ነበሩ ብለዋል”። አልጄዚራ በዘገባው የተወሰኑ ወታደሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል።

የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ኮሎኔል ፓስካል ትግሪ፥ ከዚህ አስቀድሞ “የቤኒን የመሬት እና የባህር ድንበሮች በሙሉ ለጊዜው ተዘግተዋል” ሲል የተናገረ ሲሆን፣ ዜጎች የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን “በዲሲፕሊን” ማከናወን እንዲቀጥሉ አሳስቦ ነበር።

እራሱን የዳግም ምስረታ(refoundation) ወታደራዊ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድኑ፥ በኮሚቴው ፕሬዝዳንት ሌተናል ኮሎኔል ፓስካል ትግሪ ፓትሪስ እየተመራ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ታሎን ከስልጣን ማውረዱን እና የመንግስት ተቋማትን እንዳፈረ ከገለጸ በሗላ ነበር መንግስት ምላሹን የሰጠው።

ወታደሮች መፈንቅለ መንግስቱን ከማስታወቃቸው ጥቂት ሰዓታት ሲቀረው በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን መረጃዎች ያመለክታሉ። የቀድሞ በECOWAS የግንኙነት ዳይሬክተር የነበሩት አዳማ ጋዬ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “ከባድ የተኩስ እሩምታ በፕሬዚዳንት ታሎን ቤት አቅራቢያ ላይ ተሰምቶ ነበር” ብለዋል። የፖለቲካ ተንታኙ አክለውም ከዚህ ቀደም ለፕሬዚዳንቱ ቅርብ በሆኑ ሰዎች የተመሩ ተመሳሳይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች መደረጋቸውን በመግለጽ ቤኒን ለስልጣን ሽኩቻ አዲስ እንዳልሆች ያስረዳሉ።

እ.ኤ.አ. ከ2016 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያሉት የቤኒን ፕሬዝደንት ታሎን፥ ከቀጣዩ የሚያዚያ ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ የስልጣን ዘመናቸው ያበቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር። ፕሬዝደንቱ በቦታቸው የሚተኳቸውን የእራሰቸው ፓርቲ አባል የሆኑትን፥ የገንዘብ ሚኒስትሩን ሮዋልድ ዋዳግኒን ቀድመው እጩ አድርገው ነበር። እንደ አዳማ ጌዬ ገለጻ፣ ቤኒን በፕሬዝደንት ታሎን ስር ክፍተኛ የኢኮኖሚ መነቃቃት ያሳየች ቢሆንም፥ የፕሬዝደንቁ የስልጣን ሽግግር እቅድ ዴሞክራሲያዊነት የጎደለው ነው በሚል በተቃዋሚዎቻቸው የተጠላ እርምጃ ነበር። የቤኒን መንግስት የሚታማበት የዴሞክራሲ ማሽቆልቆል ለመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ምክንያት እንደሆነ የሚያስረዱት ተንታኙ፣ ይህም ምዕራብ አፍሪካን ካጥለቀለቀው ሰፊ ወታደራዊ የስልጣን ግርሰሳ ማዕበል ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአንድ ወቅት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰፈነባቸው እና በቀጠናው የተረጋጉ ከሚባሉት አገራት አንዷ የነበረችው ቤኒን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ፍትሃዊ ያልሆኑ ምርጫዎች፣ በሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያዎች እና በፖለቲካዊ ጭቆናዎች ተፈጽመዋል የሚሉ በርካታ ውንጀላዎች የሚሰጥባት አገር ሆናለች።

በቅርቡ በኒጀር፣ ጊኒ፣ ቡርኪናፋሶ እና በጊኒ ቢሳው የመፈንቅለ መንግስቶች የተካሄዱ ሲሆን፥ በተለይም የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ከስልጣን የተወገዱበት የታህሳስ 26፥ 2025 መፈንቅለ መንግስት፥ ልክ በቤኒን እንደተሞከረው ሁሉ ወታደራዊ መኮንኖች የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣብያ ላይ ቀርበው ሥልጣን መቆጣጠራቸውን የገለጹበት ነበር።

ምዕራብ አፍሪካ፥ ፍትሃዊነት በጎደላቸው ምርጫዎች፣ በአስተዳደር ቀውሶች፣ በፀጥታ ተግዳሮቶች፣ በወጣቶች ተቃውሞዎችን እና የተሳኩ እና የከሸፉ የመንግስት መፈንቅሎችን በማሰተናገድ በከፍተኛ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ወስጥ እያለፈ ይገኛል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው