Loading...

ግብጽ ያለባትን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ውዝፍ እዳ ለነዳጅ ኩባንያዎች ልትከፍል ነው

የግብጽ የነዳጅ ሚኒስቴር በዛሬው እለት እንዳስታወቀው ሀገሪቱ ያለባትን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ውዝፍ እዳ ለአለምአቀፍ የነዳጅ ኩባንያዎች በቀጣይ ሰኔ ወር በመክፈል ቀደም ሲል ይዛው የነበረውን የመክፈያ መርሃግብር እንደምታፋጥን ተዘግቧል።

ግብጽ ያጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት በኢንቨስትመንትና በጋዝ ምርት ላይ ጫና በመፍጠሩ ምክንያት፣ ውዝፍ እዳዋ እ.ኤ.አ. በ2024 አጋማሽ ወደ 6.1 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሎ ነበር። ከእዚያ ወዲህ የእጥረት ችግሩ መ
ቢሻሻልም፣ አንድዳንድ ኩባንያዎች ውዝፍ እዳው አሁንም በድጋሚ መከማቸቱን እየገለጹ ነው።

ሀገሪቱ ባለፈው ጥር ባስቀመጠችው የውዝፍ እዳ መክፈያ መርሃግብር መሰረት መንግስት በመጭው ሰኔ ለመክፈል ያሰበው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ግብጽ ይህን ዕዳ በመክፈል የውጭ ኩባንያዎች ቁፋሮ እንዲቀጥሉ ሊያበረታታ የሚችልና እና ከ2021 ጀምሮ በፍጥነት ያሽቆለቆለውን የሀገር ውስጥ ምርት የሚያሻሽል ይሆናል። የሀገር ውስጥ ምርት መጨመር ከውጭ የምታስገባውን የኃይል መጠን ይቀንሳል።

እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት በኢራን ላይ ዘመቻ ከከፈቱ በኋላ ግብጽ ከውጭ ለምታስገባው ኃይል ትከፍል የነበረው ወጭዋ ከእጥፍ በላይ አድጓል። ወጭዋን ለመቀነስ የመንግስት ሰራተኞች ከቤት ሆነው እንዲሰሩ እና ሱቆች በሳምንት አምስት ቀናት ከምሽቱ 3 ሰዓት እንዲዘጉ ማድረግን የመሳሰሉ የኃይል ቆጣቢ እርምጃዎችን እያሰበች ነው።

የአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋም አይኤምኤፍ  እንደገለጸው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከተደጋጋሚ ቀውሶች በቅጡ ባለገገመት ሁኔታ የታየው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ውጭዋ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ገቢዋ(GDP) ከ0.2 በመቶ እስከ 0.55 በመቶ ሊሸፍን እንደማችል ተገልጿል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው