የቴዲ አፍፎ ‘ኢትዮሪካ’  በ24 ሰአት ውስጥ ከ 30 ሚሊዮን በላይ እይታ አገኘ

ዝነኛው አርቲስት ቴዲ አፍሮ(ቴዎድሮስ ካሳሁን) በትናንትናው እለት 8:ዐዐ ሰአት 18 ዘፈኖች(tracks) ያሉትን “ኢትዮሪካ” የተሰኘውን 6ኛ አልበሙን በራሱ የዩቲዩብና ሌሎች ማህበራዊ ፕላትፎርሞች ለቅቋል።

ቴዲ ረጅም ዝግጅት ተደርጎበታል የተባለውን  ይህን አልበም ያወጣው “ኢትዮጵያ” የተሰኘውን አልበም ከለቀቀለ ከ9 አመታት በኋላ ነው።  የእዚህን አልበም ስም ይፋ ካደረገበት ቀን ጀምሮ አድናቂዎቹ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠብቁት ቆይተዋል።

አልበሙ በዩቲዩብ ቻናል ከተለቀቀበት ሰአት ጀምሮ ከፍተኛ እይታ እያገኘ ነው። በተለቀቀ በ24 ሰአታት ውስጥ 30,234,000 እይታ ማግኘት ችሏል።

ከዘፈኖቹ ውስጥ “ዳስጣል” ፣ “ጀምበር”፣ እና “መሬማ” በተከታታይ 4.7 ሚሊዮን፣ 2.9 ሚሊዮንና  2 ሚሊዮን እይታ  በማግኘት ከፍተኛ ተደማጭ ሆነዋል።

ይህ አልበም ቴዲ በማህበራዊ ፕላትፎርሞች ያለውን ተደራሽነትም እንዲመነደግ አስተዋጽኦ አድርጓል ማለት ይቻላል። አልበሙ ከመለቀቀሉ በፊት ዩቲዩብ (TeddyAfroOfficial) 1.3 ሚሊዮን ሰብስክራይበርስ የነበሩት ሲሆን ከ24 ሰአት በኋላ ደግሞ 550,000 ጨምሮ 1.85 ሚሊየን ገደማ ደርሷል።

ቴዲ ከዚህ በፊት አቡጊዳ፣ ያስተሰርያል፣ ጥቁር ሰውና ኢትዮጵያ የተሰኙ ሙሉ አልበሞችንና ነጠላ ዜማዎችን የለቀቀና በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ዝነኛ ከሆኑት አርቲስቶች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው