ኬንያ የአለም ባንክ ፈጣን ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

ኬንያ የአለም ባንክ የኢራን ጦርነት ያደረሰባትን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል ፈጣን ብድር እንዲሰጣት መጠየቋን የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ተናግረዋል።

እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ከውጭ በሚገባ ነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆነች ኬንያ ቤንዚንን(petrol) ጨምሮ የሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እጥረት እንዳይከሰትና የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ጥረት እያደረገች ነው።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ኬንያ የአለም ባንክን ብድር ከጠየቁ ሀገራት ውስጥ በግልጽ መጠየቋን ይፋ ያደረገች የመጀመሪያዋ ሀገር ነች።

የአይኤምኤፍ (IMF) ኃላፊ ክሪስታሊና ጂዮርጂቫ እንደገለጹት ቢያንስ 12 ሀገራት ቀውሱን ለመቋቋም የሚያስችል የብድር ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ካሙ ቱጌ አይኤምኤፍ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ኬንያ የጠየቀችው ብድር ከፍ ያለ መሆኑን፣ ነገርግን አሀዝ አለማስቀመጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

አይኤምኤፍ ሀገራት ቀውስ በሚያጋጥማቸው ወቅት ቀውሱን እንዲቋቋሙ የፖሊሲና የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግበት ፈጣን የድጋፍ ምላሽ “Rapid Response Support” የተባለ አሰራር አለው።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይህን ቀውስ ለመቋቋም በፔትሮሊየም ምርቶች ላይ ይጣል የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ(Value Added tax) ከ13 በመቶ ወደ 8 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርገዋል። ባለፈው ሳምንት ባንኩ የ2026ን የእድገት ትንበያ ቀደም ሲል ከነበረው 5.5 በመቶ ወደ 5.3 በመቶ ዝቅ አድርጎታል። ባንኩ የኢራኑ ጦርነት በምስራቅ አፍሪካው ትልቅ ኢኮኖሚ ቁልፍ ዘርፎች ላይ አደጋ መደቀኑንም ገልጿል።

ጦርነቱ በተፋፋመበት ወቅት የሀገሪቱ መገበበያ ገንዘብ ሸልንግ በተወሰነ መጠን መዳከሙና ከእዚያ ወዲህ ግን እያንሰራራ እንደሚገኝ ገዥው ተናግረዋል።“ጫና ቢኖር.. በርእግጠኝነት ይዳከም ነበር” ያሉት ገዥው ማዕከላዊ ባንኩ እንዲህ አይነት መዋዠቅን ለመቋቋም የሚያስችል ክምችት አለው ብለዋል።
ገዥው አክለውም እንደገለጹት ማዕከላዊ ባንኩ የወርቅ ክምችት የመጨመር እቅዱን እየገፋበት ነው

በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ባንኩ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከ13 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን የ5.8 ወራትን የውጭ ግዥ የሚሸፍን ነው ተብሏል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው