Loading...

የነዳጅ ዋጋ በ7% ጨምሮ በበርሜል 126 ዶላር ደረሰ

የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ በሚወስደው አዲስ ወታደራዊ እርምጃ ዙሪያ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጻ ሊያቀርብ ነው የሚል ሪፖርት ከወጣ በኋላ የነዳጅ ዋጋ እአአ ከ2022 ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ኢራን አሜሪካ በድርድሩ ወቅት ያቀረበቻቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን እንድትቀበል የሚያስገድድ “አጭርና ከባድ” የድብደባ እቅድ እያዘጋጀ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

የብሬንት(Brent) ድፍድፍ ነዳጅ በ7 % ጨምሮ በበርሜል 126 ዶላር እየተሸጠ እንደሚገኝ ዘገባው ጠቅሷል።  የሰላም ንግግሩ ባለበት በመቆሙና ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ስርጥ እስካሁን ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ፣ የነዳጅ ዋጋ በዚህ ሳምንት እየጨመረ እንዲሄድ ምክንያት ሆኗል።
በእስያ ገበያ 126.31 ዶላር በበርሜል የተሸጠው ብሬትን አሁን ላይ ቀንሶ በአውሮፓ ገበያ 121 ዶላር በመሸጥ ላይ ነው። አንዳንድ አየርመንገዶችም የትኬት ዋጋን በመጨመር ወይም ጉዞን በመቀነስ ቀውሱን ለመቋቋም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተገለጸ ነው።

በጦርነቱ ምክንያት የተከሰተው አለምአቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ቀውስን አስከትሏል። ሀገራት ቁውሱን ለመቋቋም ነዳጅን ለመቆጠብ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እያስተዋወቁ ናቸው።

አሜሪካና ኢራን ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረው አለምአቀፍ  የነዳጀ ዋጋ አሁን ላይ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው። ሁለቱ ሀገራት ወደ ስምምነት መጥተው የአለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ የማይከፈት ከሆነ የዋጋ ጭማሪውና ይህን ተከትሎ የሚመጣው ኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንደሚከፋ ይጠበቃል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው