Loading...

በኬንያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በጊዜያዊነት ተቋረጠ

ኬንያ የትራንስፖርት አድማ

በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ተቃውሞ ከ4 ሰዎች ህይወት መጥፋትና ከ30 በላይ ሰዎች ጉዳት በኋላ ለአንድ ሳምንት በጊዜያዊነት ተቋርጧል።

ይህን ተቃውሞ የተመራው ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ የትራስፖርት ማህበራት ነው።

በኬንያ የናፍጣ ዋጋ በ23.5 በመቶ የጨመረ ሲሆን የቤንዚን ዋጋ ደግሞ የ8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አሽከርካሪዎች ይህ ጭማሪ በእነሱም ሆነ በተጓዦች ላይ ከባድ ጫና ያመጣል በሚል ነበር ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ያስነሱት።

የመንግስትና የትራንስፖርት ማህበራት ድርድር ሰኞ ከከሸፈ በኋላ፣ ተቃውሞው ማክሰኞም ቀጥሎ ነበር። ተቃዋሚዎች ጎማዎችን በማቃጠል መንገዶችን ዘግተው ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ በመግባታቸው ተጓዞች እንዲጉላሉና የትራፊክ እንቅስቃሴውም እንዲታወክ አድርጓል።

የኬንያ የሀገር የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኪፕቹምባ ሙርኮሜን መንግስት በቀጣዮቹ 7 ቀናት ውስጥ ከነዳጅ ዘርፍ ተዋናዮች ጋር ውይይት በማድረግ መፍትሄ ለማፈላለግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የትራንስፖርት ማህበሩ ተወካይ ኬኔዲ ካውንዳ በበኩላቸው ማህበሩ ለአንድ ሳምንት ተቃውሞውን በማቆም ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን ገልጸው፣ ስምምነት ካልተደረሰ ግን ቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

የኬንያ መንግስት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት ላይ የተፈጠረ ችግር እንደሆነ ያስረዳ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ግን ይህ በአንዳንድ ነጋዴዎች የትርፍ ፍላጎት የተነሳ የተፈጠረ ነው ብለዋል።

ፖሊስ በተቃውሞው ወቅት 348 ሰዎች መታሰራቸውንም አስታውቋል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው