Loading...

ስለ 2026ቱ የፊፋ አለምዋንጫ 10 ዋናዋና ነጥቦች

የ2026ቱ የፊፋ አለም ዋንጫ በዛሬው እለት ይጀመራል። በቡድን “A” ውስጥ የተመደቡት ደቡብ አፍሪካና ሜክሲኮ፣ በሜክሲኮ ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው ስታድዮ አዝቴሳ የመክፈቻ ጨዋታውን ያካሄዳሉ።

የዘንድሮው የአለምዋንጫ ብዙ ቡድኖችን በማካተት፣ በውድድር ጊዜ ርዝማኔና በሚሸፍነው የቦታ ስፋት ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ለየት ያደርገዋል። 48 ቡድኖች የሚሳተፉበትና ሶስት የሰሜን አሜሪካ ሀገራት የሚያስተናግዱት ይህ ውድድር በጥሎ ማለፉ ውድድሩና በሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት ላይ ትላልቅ ለውጥ አስተዋውቋል

የዘንድሮውን ውድድር የተመለከቱ 10 ዋናዋና ነጥቦች

-ይህ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት አስተናጋጅነት ይካሄዳል።አሜሪካ፣ ካናዳና ሜክሲኮ በጋራ ያዘጋጁታል።

-የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ወደ 48 ቡድኖች ከፍ ብሏል። የተሳታፊዎች ቁጥር ከ32 ወደ 48 ከፍ ማለቱ ተጨማሪ ብሔራዊ ቡድኖች ለመሳተፍ እድል እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

-104 ጨዋታዎች፦ የተሳታፊ ቡድኖች መጨመር የአጠቃላይ ጨዋታዎችን ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበሩት 64 ጨዋታዎች ወደ 104 ከፍ የሚያደርግ ሲሆን ውድድሩ የሚቆይበት የጊዜ ርዝማኔም አንድ ወር ከዘጠኝ ቀን(39 ቀናት) እንዲሆን ተደርጓል።

-አዲስ የጥሎ ማለፍ ዙር፦ ብሔራዊ ቡድኖች እያንዳንዳቸው አራት አባላት ወዳሉት 12 ምድቦች ተደልድለዋል። ከእያንዳንዱ ቡድን ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ሁለት ቡድኖች እንዲሁም ምርጥ ሶስተኛው የሆኑ ስምንት ቡድኖች 32 ቡድኖች ወደአሉበት ዙር ያልፋሉ።

-ዝነኛ የመክፈቻ ስቴድየም፦ የመክፈቻ ጨዋታው በሜክሲኮ ከተማ በሚገኘው ዝነኛው ስታድዮ አዝቴካ ይካሄዳል። ይህ ስቴድየም የወንዶችን የአለምዋንጫ ውድድር (1970፣1986 እና 2026) መክፈቻ ጨዋታ በማስተናገድ የመጀመሪያ ይሆናል።

-16 አስተናጋጅ ከተሞች፦ ይህ ውድድር በበርካታ የሰአት ክልል(time zones) እና በብዙ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ውስጥ በሚገኙ 16 ከተሞች መካሄዱ ከዚህ በፊት ከነበሩት የተለየ ያደርገዋል። ይህ ጉዞ ለሚያደርጉ ቡድኖች የሎጂስቲክ ችግር እንደሚሆንባቸው ተገምቷል።

-ክብረወሰን የሰበረ ሽልማት፦ ፊፋ ለአጠቃላይ የውድድሩ ሽልማት የሚውል ክብረወሰን የሰበረ 727 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አድርጓል። የውድድሩ አሸናፊ የ 50 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ይበረከትለታል።

-አዳዲስ ተሳታፊዎች፦ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር እንዲጨምር መደረጉ፣ በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩ በርካታ ሀገራት የመሳተፍ እድል እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

-የፍጻሜ ጨዋታ የሚደረግበት ቦታ፦ የጨዋታው ፍጻሜ በአሜሪካ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጀርሲ ስቴድየም እንደሚካሄድ የጨዋታው መርሃግብር ያሳያል።

-በመዝናኛ ላይ ትኩረት ይደረጋል፦ በሱፐር ቦውል(Super Bowl) የመዝናኛ አቀራረብ የተነሳሳው ፊፋ፣ በፍጻሜ ጨዋታው የእረፍት ሰአት ላይ ግዙፍ የሙዚቃ ደግስ ለማካተት አቅዷል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው