Loading...

የቻይናና አፍሪካ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትብብር

170,000 meter square meter China-Africa Industrial Park, Hangzhou

ቻይና እ.ኤ.አ. በ2000 የአፍሪካ-ቻይና ትብብር ከተመሰረተ ጀምሮ ያደረገችው ተሳትፎ በአፍሪካ ኢንደስትሪ እድገት ላይ ጉልህ የሚባል አስዋጽኦ አበርክቷል። አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ እስከ 1960ዎቹ ድረስ በአውሮፖውያን ቅኝ ግዛት ስር ስለነበሩ የራሳቸው የኢንዱስትሪ አብዮት አልነበራቸው፤ በተቃራኒው የሰው ኃይላቸውና ሀብታቸው ሌላ ቦታ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ይውል ነበር።

አፍሪካውን ሁል ጊዜ በአውሮፓውያን ጥቅም ላይ የዋሉ ተክኖሎጂዎች ከመጠቀም ውጭ በራሳቸው ለመስራት ሙከራ ቢኖርም ረጅም ርቀት መሄድ አልቻሉም። ይህ አፍሪካውያን ለምን የራሳቸውን ኢንዱትሪያላይዜሽን ህልም ማሳካት ተሳናቸው የሚል ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል

ያልጠናው የአፍሪካ ኢንዱስትሪ ዘርፉ በራሱ ብዙ ርቀት መሄድ እንደማይችል የተረዱት ሀገራት አቅም ያለው አጋር ሲፈልጉ ቆይተዋል። በዚያ ወሳኝ ወቅት አስተማማኝና ፍቃደኛ አጋር ሆና የተገችው ቻይና ናት

ኢንዱስትሪዎች ለጂዲፒ ያላቸውን አበርክቶ ከማሳደግ ባሻገር ለአፍሪካውያን አስፈላጊውን ችሎታና እውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ጥረት ተደርጓል።

የሳውዝ-ሳውዝ ሀገራት ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር እንዳልካቸው ስሜ ቻይና በአለም በኢኮኖሚ ቀዳሚ ያደረጋትን የተግባር ችሎታ ፈጣን ለሆነው የሰውኃይል ማስተላለፍ ትችላለች ብለዋል።

የቻይና-አፍሪካ ግንኙት ወቅታዊ መሆኑን የገለጹት ዶክተር እንዳልካቸው ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሺየቲቭ(ቢአርአይ) መሰረተልማት ከመገንባት ለአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን እውቀት መር ወደሆነ ትብብር ማድረግ ተሸጋግሯል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት

ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተሰሩት የኢንዱሰትሪ ፓርኮች፣ ቻይና በአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ላይ ያላትን ግዙፍ ተሳትፎ የሚያሳዩ ናቸው። እነዚህ ፖርኮች በአንድ ጊዜ ብዙ ኢንዱስትሪዎችን እንዲይዙ ሆነው የተሰሩ ናቸው።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በቻይና ተሳትፎ 60 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋል። እ.አ.አ 2023 ድረስ ቻይና በኢንዱስትሪ ፖርኮችና ከፖርኮች ውጭ ባደረገችው ኢንቨስትመንት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የስራ እድሎች ተፈጥረዋል። የቻይና የኢንዱሰትሪ ፓርክ ኢንቨስትመንት ቁልፍ ትኩረት በሆነችው ኢትዮጵያ  ብቻ 150 ሺህ ሰዎች የስራ እድል አግኝተዋል።


ከኢትዮጵያ እስከ ናይጀሪያ፣ ከካይሮ እስከ ደቡብ አፍሪካ በቻይና የተገነቡ ጨርቃጨርቅ፣ መድኃኒት፣ የቆዳ ውጤቶች የሚያመርቱ የኢንደስትሪ ፓርኮች እየተስፋፉ ናቸው። ይህም የአፍሪካን የኢንዱሰትሪ አቅም በማጎሎበት ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ገቢ(ጂዲፒ) ቁልፍ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ያደርጋል። በዚህ አመት ዘርፉ 25-30 በመቶ ገደማ የሚሆነውን የአፍሪካ ጂዲፒ ይሸፍናል ተብሏል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው