Loading...

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ሰለባ ቤተሰቦች የ29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፈላቸው

Family of Ethiopian Airlines Boeing 737 max crash victim compensated USD 29 million

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን መከስከስ አደጋ ሰለባ የሆነው የአለም የምግብ ድርጅት ኢንጂነር ቤተሰቦች የ29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው የአሜሪካ ፍርድ ቤት ወሰነ

አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ እያቀነ በነበረበት ወቅት ጥቂት እንደተጓዘ በመሾፍቱ አካባቢ የተከሰከሰው እአአ በ2019 ነበር

አየርላንዳዊው የ 39 አመቱ ሚካኤል ርያን በኢቦላ ቀውስ ወቅት ጭምር በላይቤሪያና በኢትዮጵያ ሲሰራ ቆይቷል። በአደጋው 32 ኬንያዊውንና ዘጠኝ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የ 157 ሰዎች ህይወታቸው አሎፏል።

ቦይንግ አብዛኞቹን ጥያቄዎች ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር ባደረገው የግል ድርድር ስምምነት ላይ ደርሷል። እአአ በ2020 አንድ ኬንያዊ ቤተሰብ የ3 ሚሊዮን ዶላር ለመቀበል ሲስማማ፣ ራያን ግን ጉዳዩን ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት ወስዶ ሲከራከር ቆይቶ በመጨረሻም የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቶለታል።

የአሜሪካ ፍርድ ቤት ባለፈው ግንቦት ወር ለአሜሪካዊው ሳሚያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር ካስ እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው