Loading...

የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያን 5ዐ በመቶ የኃይል ማመንጨት አቅም መሸፈኑ ተገለጸ

በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ከምታመነጨው ሀይል 50 በመቶ መሸፈኑን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ሸገር ሬድዮን ጠቅሶ ዘግቧል።

እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያ በ2018 ዓ.ም ካመነጨችው 35, 671 ጊጋ ዋት ኃይል ውስጥ ግማሽ ገደማ ያህሉ (18,360) ሜጋ ዋት የመነጨው ከህዳሴው ግድብ ነው።

ግድቡ በቂ ውሃ በመያዙና ኃይል ማመንጫ ተርባይኖቹ በሙሉ አቅማቸው በመስራታቸው ምክንያት የመነጨው ኃይል ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ዘገባው ጠቅሷል። ይህ ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ካቀረበችው ኃይል ያገኘች ገቢ ባለፈው አመት ከነበረው 75 ቢሊዮን ብር  ወደ 121 ቢሊዮን ብር ከፍ አድርጎታል።

ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ኬንያ፣ ጅቡቲና ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ነው። እአአ በ2025/2026 የበጀት አመት ለጎረቤት ሀገራት ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ኃይል 140 ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች። ኬንያ 86 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል በመግዛት ቀደሚ ሆናለች። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለዳታ ሴንተርና ክሪብቶ ማይኒንግ ከሸጠው ኃይል ደግሞ 335.5 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝቷል።

ኢትዮጵያ፣ ከግብጽና ሱዳን ጋር የውሃ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ያስገባት ግድቡ በይፋ ተመርቆ ስራ የጀመረው ባለፈው መስከረም ወር ነበር።  ግድቡ በይፋ ተመርቆ ስራ የጀመረው ከ14 አመታት ግንባታ በኋላ ነው።

ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ግድቡ ከተጀመረ አንስቶ፣ በግድቡ ግንባታ፣ ውሃ ሙሌትና አስተዳደር ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ግን ሊቋጭ አልቻለም። ግድቡ በይፋ ከተመረቀ በኋላ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ለድርድር የመቀመጥ ፍሊጎት እንደሌላት መግለጿ ውጥረቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ማየሉን የሚጠቁም ነው።

ግብጽ ግድቡ በውሃ ደህንነቷ ላይ የተጋረጠ አደጋ አድርጋ እንደምትመለከተው በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች። ኢትዮጵያ በአንጻሩ ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉልህ ተጽእኖ እንደማይኖረውና ለልማት አለማ ብቻ የሚውል ፕሮጀክት መሆኑን እንዲሁ በአጽንኦት ስትገልጽ ትደመጣለች።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው