Loading...

ክርስቲያኖ ሮናልዶና ጆርጅና ሮድሪጊዝ 10 አመታት አብረው ከቆዩ በኋላ በይፋ ጋብቻቸውን ፈጸሙ

የእግርኳሱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የረጅም ጊዜ ጓደኛው ከሆነችውና ከሞዴሏ ጅርጅና ሮድሪጊዝ ጋር በፖርቱጋል በተካሄደው ስነስርዓት በይፋ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል

ፖርቹጋላዊው አጥቂ፣ እጁን በጆርጅና እጅ ላይ አድርጎ ቀለበት አስረው የሚያሳይ ምስል በኢንስታግራም ገጹ አጋርቷል። ጋብቻውን የአመቱ ምርጥ ሲሉ የጠሩት የፖርቹጋል ሚዲያዎች ጥንዶቹ በትናንትናው እለት በሊዝበን አቅርቢያ በምትገኘው የወደብ ከተማ ካሲያስ  አምስት ልጆቻቸው በተገኙበት ቀለበት ማሰራቸውን ዘግበዋል። የኢንስታግራም ምስሉ ፖስት በተደረገ በ30 ደቂቃ ውስጥ 3 ሚሊዮን ጊዜ ተወዷል።

ጥንዶቹ በማድሪድ ጆርጅና በምትስራበት የጁሲ ሱቅ ከተገናኙ በኋላ ለ10 አመታት አብረው ቆይተዋል። በወቅቱ ሮናልዶ ለስፔኑ የማድሪድ ክለብ ይጫወት ነበር

ሮናልዶ አምስት ልጆች ያሉት ሲሆን ሁለቱ ከጆርጅና የተወለዱ ናቸው። ጆርጅና የሮናልድ የብቻው የሆኑትን ሶስት ልጇች በማሳደግ አስተዋጽኦ አድርጋለች። ሮናልዶ ወደ ሳኡዲ ሱፐርሊግ ከተዛወረ በኋላ ቤተሰቡ በአጠቃላይ በሳኡዲ ዋና ከተማ ሪያድ እየኖረ ነው።

ሮናልዶ በስፖርት ዘመኑ ለሊዝበን ክለብ ስፖርቲንግ፣ ለማንቸስተር ዩናይትድ፣ ለሪያል ማድሪድ፣ ለጁቬንቱስ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ ለሚገኘው አል-ናስር እና ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል። በሙያ ዘመኑም ወደ 1,000 የሚጠጉ ጎሎችንም አስቆጥሯል።

የ41 ዓመቱ ሮናልዶ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ካፒቴን ሲሆን በወንዶች የዓለም ዋንጫ ውድድር ስድስት ጊዜ የተሳተፈ ተጫዋች በመሆን ከአርጀንቲናው ሊዮኔል ሜሲ ጋር የጋራ ሪከርድ ይይዛል።
ሮናልዶ የባሎንዶር ሽልማትን አምስት ጊዜ አሸንፏል። ይህም በስምንት ሽልማቶች ከሚመራው ሜሲ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።

እአአ በ2022 አል-ናስርን የተቀላቀለው ሮናልዶ ባለፈው ዓመት ከክለቡ ጋር የሁለት ዓመት የውል ማራዘሚያ ተፈራርሟል። ይህ እስከ 2027 ድረስ በሪያድ እንዲቆይ ያስችለዋል ማለት ነው።
ባለፈው ዓመት የብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ የሮናልዶን ሀብት በ1.4 ቢሊዮን ዶላር ገምቶት ነበር፤ በዚህም ቢሊየነር የሆነ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው