Loading...

ድምጸ ወያኔ ጣቢያ ስም ቀይሮ ስርጭት እንዲጀምር ፈቃድ መስጠቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ

Dimtsi weyane Tigray to broadcast under new name Maedot Broadcasting Service

የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድምጸ ወያኔ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስሙን ወደ “ማዕዶት ብሮድካስቲንግ አገልግሎት” መቀየሩንና የስርጭት ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል።

ጣቢያው ቀደም ሲል “የጦርነት መሳሪያ ሆኖ” እያገለገለ ነው በሚል የስርጥት ፈቃዱ መሰረዙን የገለጸው ባለስልጣኑ አሁን ላይ ክልሉን የሚመራው ባለአደራ አስተዳደር ሰላምና መረጋጋት እንዲያረጋግጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ፈቃድ ተሰጥቶታል ብሏል።

ባለፈው ወር በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በህወሓትና በፌደራል መንግስት በድጋሚ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል መንግስት የክልሉን ዋና ከተማ መቀሌንና በርካታ ከተሞችን ተቆጣጥሯል።

በክልሉ ስላምና መረጋጋት፣ የህዝብ አገልግሎቶች እንዲመለሱ እንዲሁም ለምርጫ አስቻይ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ የሚያደርግ ለስድስት ወራት የሚቆይ በፌደራል መንግስት የሚመራ የባለአደራ አስተዳደር መቋቋሙ ይታወሳል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው