Loading...

ሳኡዲ አረቢያ፣ ፓኪስታንና ቱርክ የኔቶ አይነት  የጋራ የመከላከያ ጥምረት ፈጠሩ

Saudi Arabia, Pakistan and Turkey agree to NATO-style mutual defense pact amid escalating Iran conflict.

ሳኡዲ አረቢያ፣ ፓኪስታንና ቱርክ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚደርስን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት የሚያስችል የኔቶ አይነት የጋራ የመከላከያ ስምምነት በዛሬው እለት በሳኡዲ አረቢያ መካ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ከሶስቱ ሀገራት በአንዳቸው ላይ የሚቃጣ ጥቃት “በሁለም ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል” የሚል ይዘት ያለው መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል

ይህ ስምምነት የተደረሰው፣ ሳኡዲ አረቢያ ከበርካታ ግንባሮች ጥቃት በተቃጣባትና ጥቃት ቢፈጸምባት ጣልቃ ለመግባት የሚያስገድድ ሁኔታ ባለበት ወቅት ነው። ሀገራቱ ባወጡት የጋራ መግለጫ እንደገለጹት ስምምነቱ ጥቃትን በጋራ ለመከላከልና በመካከላቸው ያለውን ሁሉንአቀፍ የመከላከያ ትብብር ለማሻሻል ያለመም ነው

ስምምነቱ በእስልምና ሃይማኖት ዘንድ ቅዱስ በሆነችው መካ መፈረሙ፣ ሃይማኖታዊና ፖለቲካ እንድምታ ይኖረዋል ተብሏል።

ሳኡዲ አረቢያ በአለም ቀዳሚ ከሆኑት የነዳጅ ላኪዎች አንዷ ስትሆን ፓኪስታን ደግሞ ኑክሌር የታጠቀች ብቸኛዋ የሙስሊም ሀገር ነች። ስምምነቱ የተደረሰው የቱርኩ ፕሬዝዳንት ታይፕ ኤርዶኻን፣ የሳኡዲው ልኡል አልጋወራሽ ሞሀመድ ቢን ሳልማን እና የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሻሪፍ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው