Loading...

አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኤር ኢንዲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተቀጠሩ

Air India hires former ethiopian Airlines CEO Tewelde Gebremaryam

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የህንዱ ኤየር ኢንዲያ ዋና ስራ አስፈጻሚና ማኔጂንግ ዳሬክተር ሆነው መቀጠራቸውን ኤየር ኢንዲያ በጽረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ባለፈው ወር አቶ ተወልደ የፓኪስታን አለምአቀፍ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መቀጠራቸውን የሚገልጹ የሚዲያ ዘገባዎች ወጥተው የነበረ ቢሆንም መዳረሻቸው ኤየር ኢንዲያ ሆኗል

አቶ ተወልደ በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩትን ካምቤል ዊልሰንን ይተካሉ።

አየርመንገዱ እንዳስታወቀው የኤየር ኢንዲያ ቦርድ ከመላው አለም ያመለከቱ እጩዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኋላ አቶ ተወልድ ብቁ ሆነው አግኝቷቸዋል። በግምገማው መሰረት አቶ ተወልደ ለኤየር አንዲያ የሚሆን ስትራቴጂካዊ አፈጻጸምና የአመራር አቅም እንዲሁም በዘርፉ ያላቸው ልምድ ተመራጭ ተደርገዋል።

ከአስርት አመታት በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ በአፍሪካ በዘርፉ ስኬታማ ከሚባሉት የአቪዬሽን ሰው ተጠቃሽ ናቸው። አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ አየርመንድ ገቢ እንዲጨምር፣ አለምአቀፍ መዳረሻዎቹና አጠቃላይ ያሉት የአውሮፕላኖች ቁጥር በሶስት እጥፍ ገደማ እንዲጨምሮ አስተዋፅኦ ማድረጋቸው ይነገርላቸዋል

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው