Loading...

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ለማስተናገድ የሚያስችላትን ይፋዊ የጨረታ ሰነድ ለካፍ (CAF) አስገባች

Ethiopia submitted bid handbook to CAF for 2028 AFCON

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በመተባበር የ2028ቱን የ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2028) ለማስተናገድ የሚያስችለውን አጠቃላይ የጨረታ ሰነድ (Bid Handbook) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) በይፋ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ታላቁን አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ያላትን ቀዳሚ መሪነት ዳግም ለማደስ ዝግጁ መሆኗን በሰነዱ አረጋግጣለች።

ለካፍ ገቢ የተደረገው የጨረታ ሰነድ ሀገሪቱ ውድድሩን ለማስተናገድ ያላትን ዝግጁነት የሚያሳዩ በርካታ መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው፦

  • የስቴዲየሞች እና ልምምድ ሜዳዎች መሠረተ ልማት፦ በግንባታ እና በማደስ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስቴዲየሞች እና የስልጠና ስፍራዎች ዝርዝር፤
  • የአቪዬሽን እና የሆቴል አቅም፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለውን አህጉራዊ የትራንስፖርት ትስስር እና የከተሞች የሆቴልና የሆስፒታሊቲ አቅም፤
  • የመንግሥት ዋስትና (Government Guarantee)፦ የኢፌዴሪ መንግሥት ለውድድሩ ስኬታማነት አስፈላጊውን የደህንነት፣ የፋይናንስ እና የሎጂስቲክስ ዋስትና መስጠቱን የሚያረጋግጡ ይፋዊ ደብዳቤዎች።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስራች ሀገራት አንዷ ስትሆን፣ እ.ኤ.አ. በ1962፣ በ1968 እና በ1976 የአፍሪካ ዋንጫን በስኬት ማስተናገዷ ይታወሳል። የ2028ቱን ማስተናገድ ካሸነፈች ከ50 ዓመታት በኋላ ውድድሩን ወደ ምስራቅ አፍሪካ ምድር ዳግም የምታመጣ ይሆናል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው