በአለም የቴክኖሎጂ ፉክክር ግንባር ቀደም ተሳታፊ የሆነችው ቻይና የሮቦት የሩጫ ሙከራ አካሂዳለች።
በቻይናው ስማርትስልክ ሰሪ ኩባንያ ሆነር የተሰራው ሮቦት(ሁማኖይድ ሮቦት) 100 ሜትር ርቀትን በ9.32 ደቂቃ በመሮጥ በጃማይካዊ ፈጣን ሯጭ ሁሴን ቦልት ተይዞ የነበረው ሪከርድ መስበሩን የቻይና መንግስት ሚዲያዎችን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል።
ብልጭታ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሮቦት በመጭው ቅዳሜ በቻይና ቤጂንግ ለሚካሄደው የአለም ሮቦት ውድድር ዝግጅት ላይ በተደረገው ሙከራ 14.3 ሜትር በሰአት በመሮጥ ፈጣን ሰአት አስመዝግቧል። ይህ ውጤት ቦልት በ2009 በጀርመን በርሊን በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮንሽፕ ላይ ካስመዘገበው የ9.58 ሰከንድ የወንዶች የ100 ሜትር ሪከርድ የበለጠ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ቻይና ለሮቦት(ሁማኖይድ ሮቦት) ከፍተኛ ትኩረት የሰጠች ሲሆን ፖሊሲ አውጭዎችና ኩባንያዎችም በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ)ና ሀርድዌር ዘርፍ የሚኖር እድገት በማንፋክቸሪንግ፣ በሎጂስቲክና በደንበኞች ተጠቃሚነት ላይ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት አሳድረዋል።
ይህ ሮቦት ባለፈው ሚያዝያ በቤጂንግ የተዘጋጀውን የግማሽ ማራቶን በ50 ደቂቃ በመጨረስ ፈጣን ሰአት ማስመዝገቡ ይታወሳል። በማራቶን ላይ የሮጠው ሮቦት 169 ሴንቲሜትር ቁመትና 95 ሳንቲም እግር ያለው እንደነበር ተገልጿል።
ነገርግን ተመራማሪዎች ለአለም የሮቦት ውድድር በሚሆን መልኩ እግሩን በ10 ሳንቲም ከፍ በማድረግ 105 ሳንቲሜትር አድርገውታል።











