Loading...

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከ 4 አመታት በኋላ ስራውን አጠናቀቀ

Ethiopia's National Dialogue Commission has commenced after four years

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአራት አመታት በኋላ በዛሬው እለት ተልእኮውን ማመጠናቀቁ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።

ኮሚሽኑ ስራውን ያጠናቀቀው ከመላ ሀገሪቱ የተሰባሰቡ ከ 4000 በላይ ተወካዮች በተመረጡ ስምንት አጀንዳዎች ላይ በአዲስ አበባ ለሳምንታት የምክክር ጉባኤ ካደረጉ በኋላ ነው

ምክክሩ በስኬት መጠናቀቁን ለማብሰር በተደካሄውና በመንግስት የመገናኛ ብዙኻን በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም የውጭ እንግዶች ተገኝተዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ይህ ጉባኤ ችግሮችን የመፍቻ ጅማሮ እንጂ ማብቂያ አለመሆኑን ገልጸዋል

“ችግሮች የሚፈቱት ከተወያየንና ከተደማመጥን ብቻ ነው ያሉት” ፕሮፌሰሩ ተመካካሪዎቹ ያነሷቸው አጀንዳዎችና ወሳኔዎች ወደ የመጡት ክልልና ከተማ አስተዳድሮች ይላካሉ ብለዋል።

ተመካካሪዎቹ ወሳኔ የደረሱባቸው ነጥቦች ጉባኤው ማጠቃላያ ላይ እንደተነበቡላቸው ቢገለጽም፣ ዝርዝር ይዘቶቹ ግን እስካሁን በይፋ አልታተሙም።

ፕሬዝደንት ታየ አጽቀስላሴ፣ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም ኮሚሽነሮች 46 ቀናትን የፈጀው ጉባኤ ስኬታማ መሆኑን ተናግረዋል።

በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ  አብንና እናት የተባሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ላይ ጣልቃገብነቶችና የአንድ ቡድን ፍላጎት የመጫን ጥረት ተደርጓል የሚል አቤቱታ አሰምተዋል። ነገርግን ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ክስ አስተባብለዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው