Loading...

ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን ሪከርድን ሰበረ

Kejelcha breaks men's half marathon world record by 29 seconds

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቦነስ አየርስ በተካሄደው አለምአቀፍ የጎዳና አትሌቲክስ ውድድር ግማሽ ማራቶንን በ56 ደቂቃ 51 ሰከንድ በመጨረሽ ሪከርድ መስበር ችሏል።

የ29 ዓመቱ አትሌት እአአ በጥቅምት 2024 በስፔን ቫሌንሲያ 57 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት ነበር  የዓለም ሪከርድ የያዘው። ሆኖም በመጋቢት ወር በኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ ተነጥቆ ነበር

ኪፕሊሞ በዚህ ዓመት መጀመሪያ በሊዝበን 57 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በመሮጥ ክብረ ወሰኑን አስመዝግቦ ነበር። ዮሚፍ ይህንን ሰአት በ 29 ሰከንድ በማሻሻል ሪከርዱን መልሶ በእጁ አስጠብቷል

በ10,000 ሜትር የዓለም የትራክ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ዮሚፍ፣ በወንዶች 10,000 ሜትር ለጎዳና ላይ ውድድርም የዓለም ሪከርድ ባለቤት ነው።

በተጨማሪም በዚህ ዓመት በለንደን ማራቶን በመወዳደር ከሁለት ሰዓት በታች ማራቶን ከሮጡ የመጀመሪያ አትሌቶች አንዱ ሆኗል። በውድድሩ ከኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ነበር ያጠናቀቀው።ሳዌ ዮሚፍን በ11 ሰከንድ በመብለጥ  በ1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት ነው ሪከርድ የሰበረው።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው