Loading...

የአሜሪካ መንግስት እስከ 200,000 የሚደርሱ የውጭ ዜጎችን ቪዛ ለመሰረዝ ማቀዱን ባለስልጣናት ተናገሩ

Trump administration to revoke upto 200,000 visa applications

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ጥገኝነት የጠየቁ ወይም ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ ያሉ እስከ 200,000 የሚደርሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን የንግድና የጉብኝት ቪዛ ለመሰረዝ እየተዘጋጀ መሆኑን ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

ይህ እቅድ ተፈጻሚ ከሆነ በአሜሪካ ታሪክ በአንድ ጊዜ የተደረገ ትልቁ የቪዛ ስረዛ ሊሆን እንደሚችልና የህግ መሰናክሎች ሊያጋጥሙት እንደሚችል ኤፒ ዘግቧል

ኤፒ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰነዶችን ጠቅሶ እንዘገበው ከሆነ ዕቅዱ በህግ ካልታገደ ወይም ከልተቀለበሰ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እአአ ከ2016 እስከ 2026 የተሰጡ የB1 እና B2 የስራ ቪዛዎችን እንደሚሰርዝ በቀጣዮቹ ሳምንታት ይፋ ሊያደርግ እንደሚችል ይጠበቃል። ይህም ጥገኝነት የጠየቁ ወይም አሁን በመጠየቅ ላይ ያሉ የቪዛ ባለቤቶችን ያካትታል ተብሏል
እርምጃው የሚወሰደው ከሀገር ደህንነት መሥሪያ ቤት ጋር በመቀናጀት ነው ተብሏል።

“ወደ አሜሪካ ለአጭር ጊዜ ጉብኝት ብለው ከገቡ በኋላ በቋሚነት ለመቆየት ጥገኝነት የጠየቁ የውጭ ዜጎችን ለመለየትና የስደተኛ ያልሆኑ(nonimmigrant) ቪዛዎቻቸውን ከደህነነት መስሪያቤት ጋር እየተቀናጀን ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት ገልጸዋል።
ባለሥልጣናቱ የቪዛ ስረዛው ወዲያውኑ ከአሜሪካ መባረርን የሚያስከትል እንደማይሆን ገልጸዋል። የጥገኝነት ጥያቄያቸው በሂደት ላይ ያለው እነዚህ ሰዎች የቪዛ ምድባቸው ይቀየራል፤ የንግድ ወይም የጎብኚ ቪዛ ባለቤትነታቸውን ያጣሉ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሁለተኛውን የስልጣን ዘመናቸው ከያዙ ወዲህ፣ አስተዳደራቸው በቪዛ አመልካቾች ላይ ገደቦችን እያጠናከረ መጥቷል። ከእነዚህ እርምጃዎች ውስጥ የቪዛ አመልካቾችን ስለማኅበራዊ ሚዲያ ታሪካቸው ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ፣ ለቪዛ ሂደት ውድ የገንዘብ ዋስትና እንዲያስቀምጡ ማድረግ እና ለአንዳንድ ሀገሮች ዜጎች ቪዛ መስጠትን መከልከል ይገኙበታል።

የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው በሰኞ ባሰፈሩት የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክት፣ በጉብኝትና በንግድ ቪዛ ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎችን ተችተዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው