Loading...

የቻይና ተመራማሪዎች ድምፆችን መገንዘብ የሚችል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጨርቅ ፈጠሩ።

በሶቾው ዩኒቨርሲቲ ያሉ የቻይና ተመራማሪዎች A-Textile, የተባለ ለስላሳ፣ ተጣጣፊ እና ሊታጠብ የሚችል ጨርቅ ፈጥረዋል፣ ይህም ሰዉ ሰራሽ አስተውህሎት ወይንም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የድምፅ ትዕዛዞችን እስከ 97.5% ትክክለኛነት በመገንዘብ መረጃን ይሰበስባል። ይህ አዲስ የፈጠራ ጨርቅ ንግግሮችን ከልብስ የሚመነጨውን ጥቃቅን ኤሌክትሮስታቲክ ኃይል (electrostatic charges) በመጠቀም ዘመናዊ የቤት መሣሪያዎችን መቆጣጠር፣ የዳታ ክምችት አገልግሎቶችን መጠቀም እና እንደ ጉግል-ማፕ ወይም ቻትጂፒቲ ያሉ መተግበሪያዎችን መገናኘት ያለምንም ተጨማሪ መሳሪያ መጠቀም ይችላል። ይህም የዕለት ተዕለት ግልጋሎት ያላቸውን ቁሳቁሶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወደ ሁልጊዜ ተደራሽ የሆኑ ስማርት ቴክኖሎጂ ረዳቶች ይለውጣል።

(የዜና ምንጭ Xinhua News Agency/ CGTN)

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው