Loading...

ኢራን ቀጣዩዋ ቬንዙዌላ? በኢኮኖሚ ውድቀት የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ እና የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ

በኢራን በተለያዩ ከተሞች በኢኮኖሚ ውድቀት እና በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል። በተቃዋሚዎች እና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት እስካሁን ቢያንስ 10 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁኔታው እየተባባሰ ከሄደ እና ተቃዋሚዎች ከተገደሉ አሜሪካ “ተቃዋሚዎችን ለማዳን” ጣልቃ ልትገባ እንደምትችል በ Truth Social ገጻቸው ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

የኢራን ብሔራዊ ገንዘብ (ሪያል) የመግዛት አቅም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የቆለቆለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአዝማሚያ ገበያው (Open Market) 1 የአሜሪካ ዶላር እስከ 1.4 ሚሊዮን ሪያል እየተመነዘረ ይገኛል። የዋጋ ግሽበት ከ48 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ የምግብ ዋጋ ደግሞ እስከ 70 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን አገሪቱ ከምዕራባውያን ጋር በሁሉም ረገድ “የተሟላ ጦርነት” (Total War) ላይ መሆኗን ገልጸዋል።

ለኢራን የምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ አሜሪካ በተደጋጋሚ በጣለችው ማዕቀብ እንደመንስዔ ይነሳል። ሆኖም የኢራን ፕሬዝደንት ፔዢስኪያን ይህ ማለት ባለስልጣናቱን ከተወቃሽ አያድንም። ፕሬዝደንቱ በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሆነው ባለስልጣናቱ የዜጎቸን ህይወት የማሻሻል ሃላፊናታቸውን በሚገባ እንዳልተወጡ በመግለጽ የኢራንን ውስጣዊ ችግር እንደሚፈቱ ተናግረዋል፥

ፔዤስኪያን “አሜሪካ የምትቃጣው የሚሳዔል እና ቦንብ ጥቃት አንድን አገር ለማስጎንበስ በቂ አይደለም፥ እኛን ለማንበርከክ በአካል ፊት ለፊት መጋፈጥ ግድ ይላል” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኔይ፥ ለባስልጣናቱ የኢራንን የውስጥ ችግር ከውጭ ሆነው በማባበስ ለጥቅማቸው ለማዋል የሚጥሩ ሃይላትን ጸንተው እንዲጠባበቁ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

አለም አቀፍ የፖለቲካ ታዛቢዎች በናይጄሪያ እና በተለይም በቬንዙዌላ የሆነው፥ የአሜሪካ ጦር ለኢራንም የሚመለስ ሊሆን እንደማይችል አመላካች መሆኑን ይጠቁማሉ።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው