Loading...

የ2026 ዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ወጣ፤ ስዊድን እና ቱርክ ከዓመታት በኋላ ማለፋቸውን አረጋገጡ

በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያዎች ተጠናቀው በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ48ቱ ሀገራት የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰፊ ተሳትፎ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ትላንት ምሽት የተደረጉ የአውሮፓ ፕሌይ-ኦፍ (Play-off) ጨዋታዎች አስገራሚ ውጤቶችን አስመዝግበዋል።

በስቶክሆልም በተደረገው ወሳኝ የፕሌይ-ኦፍ ፍጻሜ ጨዋታ ስዊድን ፖላንድን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ትኬቷን ቆርጣለች። ለስዊድን ስኬት ትልቁን ድርሻ የተወጣው የአርሰናሉ አጥቂ ቪክቶር ዮከሬሽ ሲሆን ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩ (በ88ኛው ደቂቃ) ያስቆጠራት የማሸነፊያ ጎል ስታዲየሙን በደስታ አናውጣለች። ስዊድን በምድብ “F” ውስጥ ከኔዘርላንድስ፣ ጃፓን እና ቱንዝያ ጋር ተደልድላለች

በሌላ በኩል ቱርክ ኮሶቮን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ከ24 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዓለም ዋንጫ መግባት ችላለች። ቱርክ ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈችው እ.ኤ.አ. በ2002 (በጃፓንና ደቡብ ኮሪያ) የነበረ ሲሆን በወቅቱም ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል። ቱርክ በምድብ “D” ውስጥ ከአሜሪካ፣ ፓራጓይ እና አውስትራሊያ ጋር ትጫወታለች።

እንደ ጣሊያን ያሉ ታዋቂ ሀገራት ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

የ2026 ዓለም ዋንጫ ልዩ የሚያደርጉት ነጥቦች፦

  • ተሳታፊዎች፦ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ32 ወደ 48 ቡድኖች ከፍ ብሏል።
  • አዳዲስ ሀገራት፦ ኡዝቤኪስታን፣ ዮርዳኖስ፣ ኩራሳዎ እና ኬፕ ቨርዴ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይሳተፋሉ።
  • የአፍሪካ ተሳትፎ፦ አህጉሪቱ በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን (9 ቀጥተኛ ተሳታፊዎችን) ወደ መድረኩ ልካለች።

ትኩረት የሚስቡ የምድብ ድልድሎች፦

  • ምድብ A፦ ሜክሲኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ
  • ምድብ C፦ ብራዚል፣ ሞሮኮ፣ ሄይቲ፣ ስኮትላንድ
  • ምድብ G፦ ቤልጂየም፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ኒውዚላንድ
  • ምድብ J፦ አርጀንቲና፣ አልጄሪያ፣ ኦስትሪያ፣ ዮርዳኖስ

ውድድሩ ሰኔ 4 ቀን 2026 (June 11, 2026) በሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም በሚደረግ የመክፈቻ ጨዋታ (ሜክሲኮ ከደቡብ አፍሪካ) ይጀምራል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው