Loading...

አሜሪካ ናይጄሪያን ጨምሮ በ59 ሀገራት ላይ የ12.5% የንግድ ታሪፍ ጣለች

የአሜሪካ መንግሥት የግዳጅ የጉልበት ብዝበዛን (Forced Labor) ለመከላከል እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችን ጥብቅ ለመቆጣጠር በሚል ናይጄሪያን ጨምሮ በ59 ሀገራት ላይ የ12.5 በመቶ ተጨማሪ የንግድ ታሪፍ (Tariff) መጣሉን አስታወቀ።

ይህ የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ቢሮ (USTR) ውሳኔ 99.4 በመቶ የሚሆነውን ወደ አሜሪካ የሚገባውን አጠቃላይ የንግድ ምርት በቀጥታ የሚነካ ነው።

የአሜሪካ የንግድ ባለሥልጣናት ታሪፉን በሁለት ዋና ዋና ደረጃዎች ከፍለውታል። የመጀመሪያው የ10 በመቶ ታሪፍ ሲሆን ይህ የተጣለው እንደ አውሮፓ ኅብረት፣ ብሪታንያ እና ካናዳ ባሉ ከፊል የቁጥጥር ሥርዓት አላቸው በተባሉ የንግድ አጋሮች ላይ ነው።

ናይጄሪያ እና የተቀሩት 44 ሀገራት ግን የ12.5 በመቶ የታሪፍ ምድብ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የተጣጣመ የግዳጅ የጉልበት ብዝበዛ መከላከያ ሕግ እና ጥብቅ የቁጥጥር ስምምነት የላቸውም በሚል ነው

ይህ ውሳኔ ከናይጄሪያ ወደ አሜሪካ የሚላኩ እንደ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የግብርና ምርቶች እና አልባሳት ያሉ ቁልፍ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ ላይ ያላቸውን የዋጋ ተወዳዳሪነት በእጅጉ ይጎዳዋል።

ይህ አዲስ የታሪፍ ዕቅድ እስከ ሰኔ 29 (July 6) ድረስ ለሕዝብ አስተያየት ክፍት የሚሆን ሲሆን መደበኛው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሰሚ ችሎት ደግሞ በሰኔ 30 (July 7) ይጀመራል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው