የሰባተኛው ጠቅላላ ብሔራዊ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ የሀገሪቱ ቦታዎች ተጀምሯል።
ምርጫውን የሚመራው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ምርጫው በማለዳ መጀመሩን የሚያሳዩ ምስሎችን እያጋሩ ናቸው።
በዘንድሮ ምርጫ ከስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበልጥ 54 ሚሊዮን ህዝብ መራጭ መመዝገቡን ቦርዱ ቀደም ሲል አስታውቋል።
በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልኡክ በአዲስ አበባ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝቶ ሂደቱን ምርጫውን መከታተል ጀምሯል።













