የአሜሪካና የኢራን ባለስልጣናት ጦርነት ለማቆምና የሆርሙዝን ሰርጥ ለመክፈት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
የነዳጅ ዋጋ እንዲቀነስ ያደረገው ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት፣ ኢራንና አሜሪካ ለበርካታ አስርት አመታት ሲወዛገቡበት የቆየው፣ የኢራን የኑክሌር መርሃግብር ጉዳይ ወደፊት ተጨማሪ ድርድር እንዲደረግበት መደረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ስምምነት በማዕቀፍ ደረጃ ያለ ቢሆንም የአሜሪካና እስራኤል በጋራ በመሆኑን በኢራን ላይ የከፈቱትና በሺዎች እንዲገደሉ ምክንያት የሆነውን ጦርነት ለማስቆም የሚጠቅም ትልቅ ስኬት ተርጎ ተወስዷል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ “ከኢራን ጋር ያለው ስምምነት ተጠናቋል”ሲሉ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ጽፈዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት የአደራዳሪዋ ፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሻሪፍ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ መደረሳቸውን ከሳወቁ በኋላ ነው።
የስምምነት ሰነዱ በመጭው አርብ እለት በስዊዘርላንድ በይፋ እንደሚፈረም ሮይተርስ ዘግቧል።
ኢራን አሜሪካንና የአሜሪካን የጦር ሰፈሮች ያሉባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን ለመበቀል የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋቷ፣ የጦርነቱ ዳፋ ከቀጣናው አልፎ ኢትዮጵያን ጨምር በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ለኢኮኖሚ ጫና የሚታወስ ነው።
Amharic Facebook package








