Loading...

የኢትዮጵያ አየርመንገድ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

Ethiopian Airlines generates staggering $9.1 billion revenue, up 20 percent

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ በዘንድሮው የበጀት አመት 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መሰብሰቡን በዛሬው እለት አስታውቋል

የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ይህ ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ብልጫ አለው

ስራ አስፈጻሚው አየርመንገዱ ገቢ በመሰብሰብና አራት አዳዲስ መዳረሻዎችን በመክፈት በአመቱ ስኬታማ የሚባል አፈጻጸም አስመዝግቧል ብለዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የአየርመንገዱ አጠቃላይ አለምአቀፍ መዳረሻዎች አሁን ላይ 150 ደርሰዋል።

አየርመገዱ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በተከሰተው በነዳጅ አቅርቦት እጥረት ቢፈተንም ከፍተኛ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አቶ መስፍን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ባሉት የአውሮፕላኖችና በአለምአቀፍ የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ ነው።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው