Loading...

በኔፓል-ቲቤት ድንበር በተከሰተው ድንገተኛ ጎርፍ 150 ሰዎች ሲሞቱ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶች የደረሱበት ጠፋ

Nepal flood disaster news Amharic

በኔፓል በተከሰተው ከባድ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ምክንያት ከ150 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ ተዘግቧል።

ቢቢሲ የኔፓል የቱሪስት ቦርድን ጠቅሶ እንደዘገበው ከጠፉት ቱሪስቶች ውስጥ 100 ህንዳውያን፣ 54 አሜሪካውያን እና 33 እንግሊዛውያን እንዲሁም 100 ኔፓላውያን ይገኙበታል። አደጋው የተከሰተበት ቦታ በሃይማኖታዊ ጎብኝዎችና ቱሪስቶች(trekkers) የሚታወቅ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

የቻይና ሚዲያዎች እንደዘገቡት በቲቤት ውስጥ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ፣ 265 ሰዎች ደግሞ ጠፍተዋል ተብሏል። ከቲቤት የተገኘው ቪዲዮ ከፍተኛ ግፊት ያለው ውሃና ናዳ በድንበር ማቋረጫ ላይ ያሉ ህንጻዎችን ሲመታ ያሳያል። በደርዘን የሚቆጠሩ የኔፓል ፖሊሶችና የኃይል ስራተኞች የደረሱበት ጠፍቷል።

ባለስልጣናቱ መጀመሪያ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሆነ ቢገልጹም፣ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግን መንቀጥቀጡ በመሬት መንሸራተት ወይም ናዳ ምክንያት እንደተከሰተ ገልጿል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው