የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የፌዴራል መንግሥትና ሕወሓት በፕሪቶሪያ የደረሱትን የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ ቀደም ሲል ተጥሎበት የነበረው እገዳ እንደተነሳለት የገለጸው ባለሥልጣኑ፤ ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዱና ግጭትን የሚያባብሱ ይዘቶችን እያሰራጨ መሆኑ በመረጋገጡ ጣቢያዉ በድጋሚ መታገዱን ገልጿል።
ባለሥልጣኑ በመግለጫው፦ “የሀገርንና የሕዝብን ደኅንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነት የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ የሚዲያ ይዘት ክትትል ግምገማችን ውጤት ያረጋግጣል” ብሏል።
በተጨማሪም ማንኛውም ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ እንዳይጠቀም በጥብቅ ያሳሰበ ሲሆን፣ ይህንን መመሪያ በሚጥሱ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
Subscribe
By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.









