ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰባተኛ ዘመን የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ላይ የአዲሱን መንግሥት ካቢኔ አቅርበው አስፀድቀዋል።
22 አባላት ያሉት አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ በአብዛኛው አዳዲስ አባላትን ያካተተ ነው።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ እንዲሁም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በድጋሚ የተሾሙ ቁልፍ ባለሥልጣናት ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት የሰላም ሚኒስትር የነበሩትን መሐመድ እድሪስን በሽግሽግ የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል። ኢትዮ-ቴሌኮምን ለበርካታ ዓመታት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት ወይዘሮ ፍሬሕይወት ታምሩ ደግሞ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።
በዚህ የካቢኔ ሹመት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) በድጋሚ በትምህርት ሚኒስትርነት በተሾሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በኩል የተካተተ ሲሆን፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል ሹመት አልተሰጠውም።
በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ወቅት የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።












