Loading...

አሜሪካ ወደፊት በኢራን ላይ ለምትሰነዝረው ጥቃት “የቦምቦች እናት” የተባለውን ቦምብ ለመጠቀም እያሰበች ነው ተባለ

.S. Considers Using the “Mother of All Bombs” in a Future Attack on Iran

አሜሪካ ወደፊት በኢራን ላይ ለምትሰነዝረው ጥቃት “የቦምቦች እናት” የተባለውን ቦምብ ለመጠቀም እያሰበች ነው ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ እንደገና ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሚሰጡ ከሆነ፣ የአሜሪካ ጦር “የቦምቦች እናት” በመባል የሚታወቀውን ግዙፍ ቦምብ (GBU-43) ያካተተ ጥቃት ለመፈጸም እያቀደ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህንን ቦምብ በኢራን ላይ በሚደረግ ጥቃት መጠቀም ግጭቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሊያሳድገው እንደሚችል ዘገባው ጠቅሷል።

ባለፈው የካቲት ወር አጋማሽ አካባቢ እስራኤል ከአጋሯ አሜሪካ ጋር በመሆን በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ፈጽማ ነበር። ጥቃቱም የኢራንን ወታደራዊ አመራሮችና ከ1,000 በላይ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉ ተዘግቧል።

ኢራንም በአጸፋው ወደ እስራኤልና የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች ወደሚገኙባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሚሳይሎችንና ድሮኖችን በብዛት በመላክ የበቀል እርምጃ ወስዳለች። በኢራን ጥቃቶች የአሜሪካ ንብረቶች መውደማቸውና አንዳንድ የአሜሪካ ወታደሮች መሞታቸው ተዘግቧል።

ኢራን በዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ ውስጥ ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ በመዝጋት ቀጣናዊው ቀውስ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ እንዲኖረው አድርጋለች። በፓኪስታን አስታራቂነት በተካሄደው ድርድር ተኩስ ለማቆምና የባሕር ሰርጡን ክፍት ለማድረግ ስምምነት ቢደረስም፣ እስካሁን ተግባራዊ ውጤት አልተገኘም።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው