Loading...

በኬንያ ሁለተኛው የኢቦላ ታማሚ መኖሩ ተረጋገጠ

Kenya Reports First Imported Ebola Case as Patient Dies

ኬንያ ወደ ዲሞክራሲያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ (ዲአርሲ) ተጉዞ የተመለሰው ኬንያዊ በኢቦላ ቫይረስ መሞቱ ከተረጋገጠ ከ10 ቀናት በኋላ ሁለተኛውን ተጠቂ ማግኘቷን አረጋግጣለች።

ቢቢሲ እንደዘገበው የ39 አመቱ ይህ ታማሚ የመጀመሪያው ሰላባ የቅርብ ቤተሰብ ነበር። ይህ ታማሚ ሰኞ እለት የህመሙን ምልክት ሲያሳይ ከትናንት ማክሰኞ ጀምሮ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ስለሚገኝ የመስፋፋት እድሉ ዝቅተኛ መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የኬንያ የጤና ባለስልጣናት እንደገለጹት ህመሙን በቶሎ መለየት የታማሚውን የማገገም ሁኔታን እንደሚያሻሽልና ቫይረሱ ወደ ህብረተሰቡ እንዳይስፋፋ ለመከላከል እንደሚጠቅም ጠቅሰዋል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩት ከበርካታ ሳምንታት በኋላ በመሆኑ ቀደም ብሎ የሚደረግ ምርመራ መስፋፋቱን ለመገደብ አስፈላጊ ነው። ህዝቡ እንዲረጋጋና ነገሮችን በጥንቃቄ እንዲያይ ያሳሰቡት ባለስልጣናቱ ሁለቱ ኬዞች(ህመሞች) የተያያዙ መሆናቸውንና ወደ ማህበረሰቡ መተላለፋችን የሚያሳይ መረጃ አለመኖሩን ገልጸዋል።

የእነዚህ ታካሚዎች ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ሚኒስቴሩ የኬንያ ድንበሮች፣ የንግድ መስመሮች እና የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ክፍት መሆናቸውን እና በጉዞ ወይም በስብሰባዎች ላይ ምንም አይነት ገደብ እንደሌለ አረጋግጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመጀመሪያው ታካሚ የነካካቸውን ሰዎች የመከታተል ስራ ቀጥሏል። ከተለዩት 128 ንክኪ ካላቸው ሰዎች መካከል 113ቱ የተገኙ ሲሆን፣ 108ቱ በአሁኑ ጊዜ በኬንያ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የቀሩትን 15 ሰዎች የመከታተል ስራ ግን አሁንም ቀጥሏል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው