Loading...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያቋረጠውን የመቀሌ በረራ እንደገና ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት ሳምንታት በፊት አቋርጦት የነበረውን ወደ መቀሌ የሚያደርገውን የበረራ አገልግሎት ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እንደገና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ፣ መንገደኞች የጉዞ ቦታ ማስያዝ እንደሚችሉ ገልጿል።

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው “በወቅታዊ ሁኔታ” ምክንያት መሆኑን ቢገልጽም፣ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት የሕወሓት ኃይሎች አውሮፕላን ማረፊያውን በመቆጣጠራቸው ምክንያት በረራው መቋረጡን የውጭ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸው ይታወሳል።

የፌዴራል መንግሥት ጦር የመቀሌ ከተማንና አውሮፕላን ማረፊያውን መቆጣጠሩ ከተገለጸ ከቀናት በኋላ ነው አየር መንገዱ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ እንደገና ሊጀምር መሆኑን ያስታወቀው።

አየር መንገዱ ከመቀሌ በተጨማሪ ወደ ሽሬና አክሱም አውሮፕላን ማረፊያዎች የሚያደርጋቸውን በረራዎችም በተመሳሳይ ወቅት አቋርጦ ነበር። ሆኖም፣ እስካሁን ድረስ በረራውን እንደገና ለመጀመር ያስታወቀው ወደ መቀሌ ብቻ ነው።

በድጋሚ የተቀሰቀሰው ግጭት የአፍሪካ ቀንድና የአረብ ባህረሰላጤ ሀገራትን ጎትቶ ሊያስገባ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

ኢትዮጵያ፣ኤርትራ ከግብጽና ሱዳን ጋር በመሆን ህወሃትን ጨምሮ የሀገር ውስጥ ታጣቂዎች እየረዳች ነው የሚል ጠንከራ ክስ እያሰማች ነው። የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በትግራይ ክልል አዲግራት ማለፉን ሮይተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ኤርትራ በኢትዮጵያ በኩል የቀረቡ ክስችንም ይሁን ጦሯ ድንበር ጥሶ ገብቷል የሚለውን ሪፖርት አስተባብላለች። ግጽና ሱዳንም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እንዳልገቡ እየገጹ ናቸው።

አሁን ላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ያቋረጡት ኤርትራና ኢትዮጵያ ወደ አጠቃላይ ጦርነት እንዳይገቡ ተሰግቷል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው