Loading...

በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አሸነፈች!

አይናለም ደስታ በያመቱ በሚካሄደው የአምስተርዳም ማራቶን፥ የሴቶች ውድድር አሸናፊ ሆናለች።

ለማራቶን አዲስ የሆነችው አይናለም በ 2፡17፡37 ውድድሩን በመጨረስ፥ በአምስተርዳም የተለመደውን የኢትዮጵያውያን አሸናፊነት ታሪክ አስጠብቃለች። በውድድሩ 3ኛ ኪሎሜትር ላይ ወይም ከ1፡38፡07 ጀምሮ አራት አትሌቶች ብቻ ከፊት ሆነው ሲመሩ ነበር። አራቱም ሴት አትሌቶች ኢትዮጵያውያን ናቸው። አይናለም በአንደኛነት ስታሸንፍ፥ ከሗላዋ ብርቱካን ወልዴ፥ መቅደስ ሽመልስ እና ዋጋነሽ መካሻን አስከትላ አጠናቃለች። አይናለም ከተከታይዋ በአራት ደቂቃ ቀድማ ስትጨርስ ከቀድሞዋ የአምስተርዳም ማራቶን ሪከርድ ባለቤት ያለም-ዘርፍ የሗላ በ45 ሰከንድ ብቻ ዘግይታ ሪከርዱን ለጥቂት ሳትሰብር ቀርታለች።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው