Loading...

አትሌት ትግስት የራሷን ሪከርድ ስትሰብር፣ ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ ከ 2 ሰአት በታች በመግባት ሪከርድ ሰበረ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ በዛሬው እለት በለንደን የተካሄደውን የማራቶን ውድድር በማሸነፍ በራሷ ተይዞ የነበረውን የሴቶች ብቻ የአለም ሪከርድ(Women-Only World Record) ሰብራለች።

ትግስት የሴቶች ብቻ የአለም ሪከርድን 2:15:50 በሆነ ሰአት የሰበረችው እአአ ሚያዝያ 27፣ 2025 ነበር። ትግስት ይህን ውድድር በማሸነፍ በታሪክ  በሁሉም የማራቶን ውድድር አይነቶች ሶስተኛዋ ፈጣን ሯጭ ሆና እንድትቀጥል አስችሏታል።

ከባድ ፉክክር በታየበት በዚህ ውደድር ሁለት ኬንያዊውን አትሌቶች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።ሄለን ኦብሪና ጆይሲሊን ጀፕኮስጊ በተከታታይ 21:15:53 ሰአት እና 21:15:55 ሰአት አስመዝግበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በወንዶች የማራቶን ውድድር ሁለት ኬንያዊውንና አንድ ኢትዮጵያዊ አትሌቶች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ሰአት በታች አጠናቀዋል። ኬንያዋውያኑ ሰባስቲያን ሳዌ(1:59:30)፣ ኢሉድ ኪፕቾጌ(1:59:40) ያጠናቀቁ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ (1:59:41) ሶስተኛ ደረጃን በማያዝ አጠናቋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው