Afro-Insight News – ሩሲያ በውጭ አገራት ተቀማጭ ካደረገችው በርካታው፥ ማለትም 200 ቢሊየን ዩሮ በቤልጂየሙ ዩሮክሊር (Euroclear) የተባለው ግዙፍ ባንክ ውስጥ ይገኛል።
ሩሲያ ዩክሬንን ማጥቃት ከጀመረች ጀምሮ ይህ ገንዘብ ታግዶ ነበር።
የአውሮፓ ህብረት አገራት ገዘቡን በሩሲያ ጦር ድብደባ ክፉኛ ለተጎዳችው ዩክሬን መልሶ ማቋቋሚያ እና የጦር መሳሪያዎች መግዣነት እናውለው የሚል ሃሳብ አቅርበዋል።
የቤልጂየሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ባርት ዴ ዌቨር( Bart De Wever) ይህ ሃሳብ የአለም አቀፍ ህግን የሚጥስ እንዳልሆነ ማረጋገጫ እስካልቀረበልኝ ድረስ አልፈርምም ብለዋል።
“ይሄን ከማድረጌ በፊት ማስተማመኛ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
“ቢያንስ፥ ሩሲያ ገንዘቤ ይመለስልኝ ብላ አጥብቃ የጠየቀች ቀን አበላተ አገራቱ እዳውን ተከፋፍለው የየድርሻቸውን ለማዋጣት ሊስማሙ ይገባል” በማለት ፈርጠም ያለ ሙግት አቅርበዋል።













