Loading...

የሰሜን እዝ ጥቃት 5ኛ አመት መታሰቢያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተናገሯቸው

“እንዳይገም መቼም አንረሳውም” በሚል መፈክር በየአመቱ የሚከበረው፣ የሰሜን ዕዝ በሰሜኑ የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ በህወሃት ጦር የደረሰበት ጥቃትን የሚያስታውስ ዕለት ነው።
እኔ በህይወቴ የደነገጥኩበት እና አንገቴን የደፈሁበት ቀን ጥቅምት 24 ነው
ያሉት ፊልድ ማርሻሉ፣ በዕለቱ በሰሜን እዝ ወታደሮች ላይ/”የእራሱ ወገን” ላይ የህወሓት ወታደራዊ ሃይል የፈፀማቸው ጥቃቶች ናቸው ያሏቸውን በመዘርዘር፣ ደርጅቱ አሁንም ለሚያደርጋቸው የጦርነት ዝግጅቶች ማስጠንቀቂያዎችን አስተላልዋል።

የህወሃቱ ጀነራል ምግበ ሃይለ ሰሞኑን ያደረገው ንግግር ላይ በይበልጥ ያተኮሩት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ንግግሩ ግልጽ የጦርነት ጥሪ እንደሆነ ቆጥረውታል።

“ከሃዲዎች” በማለት የገለጿቸውን ህወሃት እና ሻዕቢያ “እስካልተነቀሉ ድረስ ኢትዮጵያዊ ሰላም አትሆንም” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰራዊት አላማ የኢትዮጵያን ጥቅም ማስጠበቅ ነው
ካሉ በኋላ የቀይ ባህር በር አጀንዳው እስካሁን ብቸኛው ያላሳካነው ጉዳያችን ነው ብለዋል።

👉 ለተጨማሪ የአፍሪካና የዓለም መረጃዎች የአፍሮ ኢንሳይት ገፆችን ይከተሉ

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው