Loading...

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፡ “ከቻይና ሉዓላዊነትን እንማራለን”

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን፥ ግዛታዊ አንድነቷን እና ህልውናን ለማረጋገጥ ቻይና ትምህርት የምትሰጥ ምሳሌ ነች ብለዋል።

ሶማሊያ የግዛት አንድነቷን የሚቃወሙ ተዋናዮችን መጋፈጥ መቀጠሏን እና መንግሥታቸውም ከቻይና ልምድ ትምህርት የሚወስድ መሆኑን ፣ የሶማሊያን የረዥም ጊዜ የአንድነት ትግል ከቻይና ታይዋን ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ አካሄድ ጋር በማነፃፀር ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ በቪላ ሶማሊያ ከሲጂቲኤን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ የተለያዩ ቁልፍ ጉዳዮችን ዳስሷል።

ታሪካዊ አውድ፡

ሶማሊያ ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረተች የመጀመሪያዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ስትሆን ቻይና የሶማሊያን አገርነት እውቅና ከሰጡ ቀደምት ሀገራት መካከል ነበረች። የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂያዊ ግንኙነት እንዳደገ ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል።

ቴክኒካዊ እና የሙያ ስልጣና ትኩረት:

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ ሶማሊያ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ቅድሚያ እንደምትሰጥ አፅንዖት ሰጥተው የቻይና የቴክኖሎጂ አቅም የሰው ሃብቷን ለማጠናከር እንደሚረዳት አመላክተዋል።

ኢኮኖሚያዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ:

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድ ቻይና ለምግብ ዋስትና የምታደርገውን ድጋፍ በተለይም የሶማሊያን ድርቅ እና የምግብ እጥረትን ከግምት ውስጥ በማስገባት አንገብጋቢው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ሶማሊያ በምግብ እራስን ለመቻል፥ ቻይና በግብርና እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የምታቀርበው ትብብር ቁልፍ መሆኑንም አስረድተዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው